ፖርቶ ኖቮ
Appearance
(ከፖርቶኖቮ የተዛወረ)
ፖርቶ ኖቮ (Porto-Novo፤ ደግሞ Hogbonou /ሆግቦኑ/፣ Adjacé /አጃሽ/ ተብሎ) የቤኒን ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1998 ዓ.ም.) 238,199 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 06°30′ ሰሜን ኬክሮስ እና 02°47′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ፖርቶ ኖቮ በድሮ 'አጃች' ሲባል የአጃ መንግሥት መቀመጫ ነበረ። የአሁኑ ስም ከፖርቱጊዝ ባርያ ፈንጋዮች በ17ኛ ክፍለ ዘመን ወጣ። እነሱ አንድ ጣቢያ እዚያ ሰርተው ነበር።
በኋለኛ ዘመን በ1855 ዓ.ም. እንግሊዞች አደጋ ስለ ጣሉ የፖርቶ ኖቮ መንግሥት የፈረንሳይ ጠባቂነትን ተቀበለ። ነገር ግን የጎረቤት ዳሆመይ መንግሥት የፈረንሳያውያንን ጥልቅ ማለት ስላልወደዱ ከሁለቱ መንግሥታት መካከል ጦርነት ሆነ። በ1875 ዓ.ም. የፈረንሳይ ባሕር ኃይል በፖርቶ ኖቮ ደረሰና ፖርቶ ኖቮ ወደ ፈረንሳይ ቅኝ አገር ወደ ዳሆመይ ተጨመረ። በ1892 ዓ.ም. የዳሆመይ መቀመጫ ሆነ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |