1 ሲጎ

ከውክፔዲያ

1 ሲጎስዊድን አፈ ታሪክ የስዊዶች ንጉሥና የሲግቱና ከተማ መሥራች ነበረ። በ1546 ዓ.ም. በኡፕሳላ ኤጲስ ቆጶስዮሓንስ ማግኑስ በታተመው የስዊድን ታሪክ መጽሐፍ እንደሚለው፣ ሲጎ ከኡቦ መሞት በኋላ ለ65 ዓመታት (2211-2146 ዓክልበ. ገደማ) እንደ ነገሠ ይባላል። ሲጎ በስዊዶች ላይ እየነገሠ ያህል 1 ኤሪክጎታውያን መሪነት ተመረጠ። ከማግኑስ መጽሐፍ በቀር ምንም ማስረጃ ባለመኖሩ ግን የአሁኑ ታሪክ ሊቃውንት ይህን እንደ እውነት አይቀበሉም።