Jump to content

2 ሑዚያ

ከውክፔዲያ

2 ሑዚያ ምናልባት ከ1458 እስከ 1438 ዓክልበ ድረስ ዓክልበ. አካባቢ ከ2 ዚዳንታ በኋላ በሐቱሳሽ (በሐቲ አገር ወይም የኬጥያውያን መንግሥት) የገዛ ንጉሥ ነበር።

አባቱ ዚዳንታ ወይም ማን እንደ ሆነ አይታወቅም። የሑዚያ ንግሥት ሹሚሪ ተባለች። የሑዚያም ኩኔይፎርም ማኅተም ይታወቃል። የቤተ መንግሥት አገልጋዮች አለቃ ስም አሪነል ይታወቃል። እንዲሁም የዘበኞች አለቃ ማዕረግ የያዘው ላሪያ በኋላም ሙዋታሊ ነበር። ይህም ሙዋታሊ በኋላ 1438 ዓክልበ ገደማ በመንፈቅለ መንግሥት ተነሥቶ ሑዚያን ገደለውና 1 ሙዋታሊ ተብሎ ነገሠ።

በዚህ ዘመን የጎረቤቱ አገር የኪዙዋትና ንጉሥ ታልዛ ሲሆን የሚታኒ ተገዥ ነበር።

ቀዳሚው
2 ዚዳንታ
ሐቲ ንጉሥ
1458-1438 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 ሙዋታሊ