Jump to content

4 ካሽቲሊያሽ

ከውክፔዲያ

4 ካሽቲሊያሽ ከ1241 እስከ 1233 ዓክልበ. ድረስ በካርዱንያሽ (ባቢሎን) ካሳዊ ንጉሥ ነበረ። በርሱ ዘመን በ2 ግምባሮች ላይ (በአሦርና በኤላም) ጦርነት ያደርግ ነበር። በመጨረሻ በ1233 ዓክልበ. የአሦር ንጉሥ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ ወርሮ አሸነፈውና ማረከው። ይህ የደረሰ በቱኩልቲ-ኒኑርታ 19ኛው ዓመት እንደ ሆነ ይታወቃል፤ ስለዚህ የአሦርም ዜና መዋዕል በትክክል ለመቆጠር ያስረዳል።