ነሐሴ ፲፮
Appearance
ነሐሴ ፲፮ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፮ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፳ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፲፱ ዕለታት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በዛሬው ዕለት በየዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን የሚጀመረውን ጾመ ፍልሰታ የሚፈቱበት ቀን ነው።
፲፰፻፶፮ ዓ/ም በጦርነት የተማረኩ ሰዎችን መብት ስለማስጠበቅና ስለማክበር የተዘጋጀው የጋራ ድንጋጌ (የጀኒቫ ኮንቬንሽን) በአሥራ ሁለት መሥራች አገሮች ተፈረመ። የቀይ መስቀል ማኅበርም አብሮ ተመሠረተ።
፲፱፻፷፬ ዓ/ም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ሸንጎ (እንግሊዝኛ፡ International Olympic Committee) ሮዴዚያን (አሁን ዚምባብዌ) በዘረኛነቷ ምክንያት አባልነቷን ሠረዘ።
፲፰፻፺፮ ዓ/ም በዘጠና ሦስት ዓመታቸው እስከሞቱ ድረስ ለሀያ ሰባት ዓመታት ቻይናን የመሩት ዶንግ ዢያው ፒንግ ተወለዱ።
፲፱፻፸ ዓ/ም የመጀመሪያው የኬንያ መሪ ፕሬዚደንት ጆሞ ኬንያታ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው አረፉ።
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/August 22