Jump to content

ሰኸምካሬ ሶንበፍ

ከውክፔዲያ
የ00:05, 1 ጁን 2014 ዕትም (ከElfalem (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

==

ሰኸምካሬ ሶንበፍ
ስሙ «ንጉሥ ሰኸምካሬ የንጉሥ አመነምሃት ልጅ» የተጻፈበት ምስል
ስሙ «ንጉሥ ሰኸምካሬ የንጉሥ አመነምሃት ልጅ» የተጻፈበት ምስል
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1816-1812 ዓክልበ.
ቀዳሚ ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ
ተከታይ ነሪካሬ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት 4 አመነምሃት?

==


ሰኸምካሬ ሶንበፍ ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1816 እስከ 1812 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የወንድሙ ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ ተከታይ ነበረ።

በግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ፣ ይህ ፈርዖን የ4 አመነምሃት ልጅና የ፩ ሶበክሆተፕ ወንድም ነበር። ሌሎች መምህሮች ግን ከተከታዩ ከሰኸምካሬ 5 አመነምሃት ጋር አንድ አድርገውታል። ራይሆልት እንደሚያስረዳው፣ ከሶንበፍ ቀጥሎና ከ፪ኛው ሰኸምካሬ በፊት ነሪካሬ የሚባለው ፈርዖን ለአጭር ዘመን ነገሠ።

በእርሱ ዘመን የ14ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ፈርዖን ያክቢም ሰኻኤንሬአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለእርሱ ተገዥ ሆኖ ነገሠ።

ቀዳሚው
ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን ተከታይ
ነሪካሬ
  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)