Jump to content

ያክቢም ሰኻኤንሬ

ከውክፔዲያ

==

ያክቢም ሰኻኤንሬ
የሰኻኤንሬ ጢንዚዛ ዕንቁ
የሰኻኤንሬ ጢንዚዛ ዕንቁ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1821-1811 ዓክልበ.
ቀዳሚ (ሶበክነፈሩ)
ተከታይ ያዓሙ ኑብዎሰሬ
ሥርወ-መንግሥት 14ኛው ሥርወ መንግሥት

==


ሰኻኤንሬ ያክቢም (ወይም ያከብሙ፣ ያኮበዓም) ግብጽን በ፪ኛው ጨለማ ዘመን (14ኛው ሥርወ መንግሥት) መጀመርያ ከ1821 እስከ 1811 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልትሥነ ቅርስ እንደሚያስረዳው፣ በንግሥት ሶበክነፈሩ ዘመን (በ1821 ዓክልበ. ግ.) የ14ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ፈርዖን ያክቢም ሰኻኤንሬ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለእርሷ ተገዥ ሆኖ ነገሠ። እነዚህ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ። በጤቤስ ፈርዖኖች ፈቃድና ስምምነት ግዛታቸው በስሜን ግብጽ የንግድ ማዕከል ሆነ፤ ይህም በብሉይ ኪዳን ጌሤም የተባለው ሀገር ነው።

አያሌ (ከ120 በላይ) የያክቢም ማህተሞች ወይም ጢንዚዞች በዚያ ወቅት በዙሪያው እንደ ገዛ ይገልጻሉ፤ እንዲሁም ከጤቤስ እና ከኩሽ መንግሥት ጋር ንግድ እንዳካሄደ መኅተሙ በነዚያ አገሮች በመገኘቱ ታውቋል።[1] ሆኖም በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ ያክቢም ከ200 ዓመታት በኋላ በ16ኛው ሥርወ መንግሥት ውስጥ ነበር የነገሠ።

13ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ ከሶበክነፈሩ በኋላ ተከተለ፤ የዚህም መጀመርያ ፈርዖን አሁን ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ እንደ ነበር ይታመናል። ግብጽ እንደገና ተከፋፍሎ ይህ ዘመን የመካከለኛው መንግሥት መጨረሻ እና የ፪ኛው ጨለማ ዘመን መጀመርያ ይቆጠራል።

iikbmw

(«ያከብሙ» በግብጽኛ አጻጻፍ)

ቀዳሚው
(ሶበክነፈሩ)
አባይ ወንዝ አፍ (ጌሤም) ፈርዖን ተከታይ
ያዓሙ ኑብዎሰሬ
  1. ^ Kim Ryholt, 1997, The Political Situation in Egypt During the Second Intermediate Period p. 112