Jump to content

ሰኸምካሬ 5 አመነምሃት

ከውክፔዲያ
የ00:05, 1 ጁን 2014 ዕትም (ከElfalem (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

==

5 አመነምሃት
በሙኒክ ሙዚየም ያለ የፈርዖን ራስ «አመነምሃት ፭» ሲባል፣ ይህ መታወቂያ ግን አልተረጋገጠም።
ሙኒክ ሙዚየም ያለ የፈርዖን ራስ «አመነምሃት ፭» ሲባል፣ ይህ መታወቂያ ግን አልተረጋገጠም።
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1811-1808 ዓክልበ.
ቀዳሚ ነሪካሬ
ተከታይ አመኒ ቀማው
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

==


5 አመነምሃት ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1811 እስከ 1808 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የነሪካሬ ተከታይ ነበረ።

የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስረዳው፣ የቶሪኖ ቀኖና የተባለው ነገሥታት ዝርዝር «ሰኸምካሬ ...[ሶንበ]ፍ...፣ ...፣ አመነምንሃት ...ሬ» ይላል። አለዚያ ለዚህ አመነምሃት የተረጋገጠ ቅርስ የለም።

አንድ ሐውልት ተገኝቶ «ንጉሥ ሰኸምካሬ የንጉሥ አመነምሃት ልጅ» ተጽፎበት ስለ ተገኘ፣ የዚህ ፭ አመነምሃት ሌላ ስም «ሰኸምካሬ» እንደ ነበር ተገመተ። ሆኖም ይህ ምስል የቀዳሚው የሰኸምካሬ ሶንበፍ ሐውልት ይመስላል። በብዙ መምህሮች አስተሳሰብ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች (ሶንበፍ እና ፭ አመነምሃት) አንድ ፈርዖን ነበሩ። «የጨለማ ዘመን» በመሆኑ ለዚሁ ወቅት የመዝገቦች ጉድለት አለ።

ቀዳሚው
ነሪካሬ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን ተከታይ
አመኒ ቀማው
  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)