Jump to content

እሽመ-ዳጋን (ኢሲን)

ከውክፔዲያ
የ05:09, 13 ጁን 2014 ዕትም (ከCodex Sinaiticus (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

እሽመ-ዳጋን ከ1850 እስከ 1833 ዓክልበ. ግድም ድረስ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ከኢሲን ሥርወ መንግሥት የሱመር ንጉሥ ነበር። ማዕረጉ በይፋ «የኡር፣ የሱመርና የአካድ ንጉሥ» ነበረ።

ሱመር ነገሥታት ዝርዝር እሽመ-ዳጋን ለ፳ (ወይም ለ፲፰) ዓመታት እንደ ገዛ ሲለን፣ ፲፯ የዓመት ስሞች ብቻ ለእርሱ ይታወቃሉ። ስሞቹ ለአረመኔ ጣኦታቱ ሥርዓት ጌጣጌጥ ወይም ሕንጻዎች ስለ መሥራቱ ናቸው እንጂ ምንም ዘመቻ ወይም ፖለቲካዊ ጉዳይ አይዘግቡም። [1] ኢሽመ-ዳጋን ኒፑርን ከአሞራውያን ወደ ሱመር መንግሥት አስመለሰ።

ቀዳሚው
ኢዲን-ዳጋን
ኢሲንና የሱመር ንጉሥ
1850-1833 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሊፒት-እሽታር
  1. ^ የእሽመ-ዳጋን ዓመት ስሞች