Jump to content

ኸንቲ-አመንቲው

ከውክፔዲያ
የ13:10, 13 ሜይ 2017 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
E15xntmn
tyw

ኸንቲ-አመንቲውግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ዘመን (3900-2763 ዓክልበ. ግድም) የፈርዖኖች (ነገሥታት) እና አማልክት ማዕረግ ነበረ። ትርጉሙ ከግብጽኛ «የምዕራባውያን ቀዳሚ» ሲሆን በዚህም «ምዕራባውያን» ማለት «ሙታን» ለማለት ነበር። ስለዚህ ማለቱ ደግሞ «የሙታን ቀዳሚ» ሊሆን ይችላል።

መጀመርያው «ኸንቲ-አመንቲው» የሆነው የፈርሮኖች ወላጅ ቅድማያት ኦሲሪስ (ግብጽኛ፦ አውሣር) ይመስላል። በግብጻውያን ትውፊቶች ዘንድ ይህን አውሣርን የገደለው ወንድሙ ሴት ሆነ።

የአውሣርም ልጅ ሔሩ (ሆሩስ) ተባለ። የአባቱን ቂም በመብቀል ሴትን (አጐቱን) እንደ ገደለ ደግሞ በትውፊቶች ይነገር ነበር። በጊዜም ላይ እንደ አማልክት ተቆጠሩ። የሔሩ ልጆች የተባሉት ግን ከሴትም እንደ ተወለዱ ይመስላል። «ደቂቃ ሔሩ» በሴት ልጆች ወገን ላይ ማሳደድን ጨመሩ። መጀመርያ ፈርዖኖች ከዚሁ «ደቂቃ ሔሩ» ወገን ነበሩ።

በፈርዖን ደን (3070-3054 ዓክልበ.) እና ቃዓ (3044-3037 ዓክልበ.) መቃብሮች ውስጥ፣ በተገኙት ማኅተሞች ላይ የ፩ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ይዘርዝራል፦ በአንዱ ማኅተም ናርመር፣ አሃ 1 ቴቲጀርጀት፣ ደን እና መርኒት ይዘረዘራሉ፣ በሌላውም ደን፣ አነጅብሰመርኸት እና ቃዓ ይዘረዘራሉ። በሁለቱ ማኅተሞች ላይ፣ ከያንዳንዱ ንጉሥ ስም በፊት «ኸንቲ-አመንቲው ሔሩ» የሚለው አርዕስት ይታያል።

የጣዖቱ ኸንቲ-አመንቲው (አውሣር) ቤተ መቅደስ በአቢዶስ ነበረ። በአንዳንድ ሊቃውንት አሳብ ኸንቲያመንቱ አንዳንዴ የሌላው ጣኦት የአኑቢስ ሞክሼ ሊሆን ቻለ።