Jump to content

ኤና ዴርግ

ከውክፔዲያ
የ12:18, 4 ሴፕቴምበር 2017 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ኤና ዴርግአይርላንድ አፈ ታሪክ ዘንድ ከ633 እስከ 621 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።

መልኩ ቀይ ወይም ደመግቡ ስለ ሆነ፣ «ዴርግ» (ቀይ) ተባለ። የዱዊ ፊን ልጅ ነበር፣ ቂም በማብቀል የአባቱን ገዳይ ሙይረዳኽ ቦልግራኽ ከገደለ በኋላ፣ በከፍተኛ ንጉሥነት ተከተለው። በዘመኑ ለመጀመርያው ጊዜ በአይርላንድ መሐለቅ እንደ ተሠራ ተጽፏል።

የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የኤና ዘመን ለ12 ዓመታት ቆየ፤ ከዚያ ከሥራዊቱ ጋር በስሊየቭ ሚሽ ተራሮች ከተስቦ አረፈ። ልጁም ሉጋይድ ያርዶን በዙፋኑ ተከተለው።

የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) እና የድሮ አቆጣጠር በመከተል፣ የኤና ዘመን ከ633 እስከ 621 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። (በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።)