Jump to content

ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ከውክፔዲያ
የ14:53, 1 ዲሴምበር 2017 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ፍራንክሊን፣ 1770 ዓም ተሳለ

ቤንጃሚን ፍራንክሊን ጃንዋሪ 17 1706 እ.ኤ.አ. - አፕሪል 17 1790 እ.ኤ.አ.፦ ከአሜሪካዊ አብዮት ጀምሮ ዜግነቱ አሜሪካዊ ሲሆን የአሜሪካ 100 ዶላር ኖት ላይ በሚገኘው ምስሉ ይታወቃል። የአሜሪካ መስራች አባቶች ከሆኑ እውቅ የሃገሪቱ ሰዎች አንዱ ነው። እኚህ ሰው ለአሜሪካ ጸሃፊ፣ ፖለቲከኛ፣ ዲፕሎማት፣ ወታደር፣ ተመራማሪ፣ ፍጥረት ፈልሳፊ ወዘተ. ነበሩ።

ፍራንክሊን ስለ ኅሊና ነጻነትና ስለ ግብረ ገብ ማስተማር የነበራቸው ፍቅር ከፍተኛ ነበረ። የአሜሪካን ሕገ መንግሥት ከነደፉት ዋና ሰዎች አንዱ ነበሩ። ካስፋፉት ምሳሌዎች መሃል «የክርስቶስን አራያ ምሰል» ("Emulate Christ") አንዱ ነው።