Jump to content

ብርጅታውን

ከውክፔዲያ
የ23:07, 29 ዲሴምበር 2017 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ብርጅታውን (Bridgetown) የባርቤዶስ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1998 ዓ.ም.) 96,578 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 13°06′ ሰሜን ኬክሮስ እና 59°37′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

እንግሊዝ አገር ሰዎች መጀመርያ በ1617 ዓ.ም. በደረሱበት ጊዜ ደሴቱ በሙሉ ወና እንደ ነበረ መዘገቡ። የድሮ ኗሪዎች የአራዋክ ሕዝብ ሲሆኑ ከደሴቱ በካሪቦች ወይም በስፓንያውያን ምክንያት ሸሽተው ነበርና። በደሴቱ የተገኘው ትልቅ ቅርሳቸው ብቻ አንድ ቀላል ድልድይ ነበር። እንግሊዞች ይህን ሲያገኙ ዙሪያውን 'ኢንዲያን ብሪጅ' (የቀይ ሕንድ ድልድይ) አሉት። ከ1646 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ ድልድይና ከተማ ሠርተው የከተማውን ስም ቅዱስ ሚካኤል (Saint Michael) አሉት። ከዚህም በኋላ ስሙ 'ብሪጅታውን' ('የድልድይ ከተማ') ሆነ።