Jump to content

ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ )

ከውክፔዲያ
የ22:02, 1 ኤፕሪል 2018 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያምኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍና የመንግሥት ሰው ነበሩ።

ለጊዜ የጅጅጋ እና የጨርጨር በአገረ ገዥነት ካገለገሉ በኋላ፣ በጅሮንድ (በኋላ ፊታውራሪ) ተክለ ሐዋርያት በ1923 ዓም ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ደራሲዎች ዋናው ሆኑ። አጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጻፉት ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ውስጥ አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ፴ «የሕገ መንግሥትን ትርጓሜ ስለ ማስረዳት።» በሙሉ ከበጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት ቃላት ጠቀሱዋቸው። በዚህም ሰዓት ለጥቂት ወሮች በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው አገለገሉ። ለጊዜም የኢትዮጵያ መላክተኛ በብሪታኒያ ሆነዋል።

ሕይወቴና ምዕራፍ ፴ ጠቃሚ የሆነ አጭር ጥቅስ ይከተላል፦

«ሰው እንዲጠቀምበት የሚፈቀድለት ነገር ሁሉ የጥቅም መብት ተብሏል። ይኸውም የጥቅም መብት በሁለት ዋና ክፍል ይለያያል።

፩ኛ ፡ የግል ጥቅም ለያንዳንዱ ሰው በነፍስ ወከፍነት ለየራሱ የሚሆን ነው።
፪ኛ ፡ የመተባበር ጥቅም ለሕዝቡ ሁሉ በሙሉ ለኢትዮጵያም ለአንድነትዋ የሚሆን ነው።
የግልም የመተባበርም አሳብ በሦስት ዓይነት ሊሆን ይችላል።
፩ኛ ፡ የትዳር ጥቅም (ሀብት)
፪ኛ ፡ የአእምሮ ጥቅም (ዕውቀት)
፫ኛ ፡ የልቡና ጥቅም (ፍቅርና ሃይማኖት)

«ለነዚህ ለተነገሩት በግልም በመተባበርም ለሚሆኑት ጥቅሞች ሁሉ ለደምሳሹ አሳብ ጃንሆይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሕግ ሰጥተዋል። ዝርዝር ለሚሆነው አሳብ ግን አማካሪዎች በምክር ቤት በጉባኤ እያሰናዱ እንዲያቀርቡላቸው ከላይ እንዳሳየነው የመንግሥት አቋቋም መሠረት ሕገ መንግሥት የተባለውን ተክለዋል።»