ካሪቡ
Appearance
ካሪቡ (Rangifer tarandus) የፈረንጅ አጋዘን አይነት ነው። ዝርያው በተለይ በካናዳ እና በሩስያ አገራት ይገኛል።
በእንግሊዝኛ እንስሳው በስሜን አሜሪካ ሲገኝ Caribou /ካሪቡ/ ይባላል። ይህ በፈረንሳይኛ በኩል ከሚግማቅኛ /ቃሊፑ/ ደረሰ። እንስሳው በአውርስያ ሲገኝ ግን፣ በእንግሊዝኛ በሌላ ስም Reindeer /ረይንዲር/ ይባላል፤ ይህም ከጥንታዊ ኖርስኛ /ሕረይን/ ደረሰ። ሆኖም ሁላቸው አንድ ዝርያ ናቸው፤ በስሜን አሜሪካ ከሚኖሩትና በአውርስያ ከሚኖሩት ካሪቡ መካከል ያሉት ልዩነቶች ጥቃቅን ብቻ ናቸው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |