ሉላያ በአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ለ6 ዓመታት (ከ1596 እስከ 1590 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ።
«የዲቃላ ልጅ» ወይም «የማንም ልጅ ያልሆነ» ይባላል፤ ስለዚህ ከቀዳሚው ባዛያ ዘመን ቀጥሎ ወይም ነጣቂ ወይም እንደራሴ እንደ ነበር ይታስባል። ተከታዩ የባዛያ ልጅ ሹ-ኒኑዓ ስለሆነ ከንጉሥ ቤተሠብ ያልሆነ እንደራሴ ነበር ሊሆን ይቻላል።
ከዚህ ዘመን ምንም ሥነ ቅርስ ወይም ሌላ መረጃ የለንም።