Jump to content

ባላ

ከውክፔዲያ
የ17:25, 30 ጁን 2020 ዕትም (ከWikiBayer (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ይህ መጣጥፍ ስለ ሥነ ሂሳባዊው መስመር ነው። ለሰዶም ንጉሥ፣ ባላ (የሰዶም ንጉሥ) ይዩ።
ቀዩ - ባላ (ፓራቦላ) ነው።
አረንጓዴው ዳይሬክትሪክስ የምንለው ቀጥተኛ መስመር ነው
የላይኛው ሰማያዊ መስመር የሚመነጭበት ነጥብ ፎከስ ይባላል
የሁለቱ ሰማያዊ መስመሮች ርዝመት እኩል ነው። ስለዚህ ቀዮቹ ነጥቦች ከአረንጓዴው ቀጥተኛ መስመርና ከፎከሱ ነጥብ እኩል ርቀት ስላሉ ቀዩ ባላ (ፓራቦላ) ነው እንላለን

ባላ (ፓራቦላ) በሂሳብ ጥናት ውስጥ የተስተካከለ የባላ ቅርጽ ያለው የሂሳብ መስመር ነው ቃል ነው። ባላ በሂሳብ እንዲህ ሲደረግ የፈጠራል፡ ባንድ ጠፍጣፋ ሜዳ ላይ አንድ ነጥብና አንድ መስመር እንውሰደ። ለዚህ ነጥብ እና ለመስመሩ እኩል ርቀት ላይ የሆኑ ነጥቦቹን በሜዳው ላይ ብንደረድር የምናገኘው ስዕል ባላ/ፓራቦላ ይሆናል ማለት ነው። ነጥቡ ፎከስ ሲባል፣ መስመሩ ዳይሬክትሪክስ ይባላል።

የባላ ቀመር በደካርት ሰንጠረዥ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለተጨማሪ ማብራሪያ ኳድራቲክ እኩልዮሽን ይመልከቱ

y = −p ዳይሬክትሪክስ መስመር ቢኖን እና ፎከሱ (p, 0) ቢሆን (xy) ደግሞ የባላው ነጥቦች ቢሆኑ፣ ከነጥቡና ከመስመሩ ያሉትን እኩል ርቀቶች ግምት ውስጥ በማስገባት ይህን እናገኛለን

ሁለቱንም ጎኖች በየራሳቸው ስናበዛና ስናስተካክል ይህን እናገኛለን

ይህን ባላ በሜዳው ሁሉ ስናዘዋውረው ይህን መልክ ይይዛል

እንግዲህ ይህ ሲስተካከል

የሰጣል። በሂሳብ ጥናአት የባላ አጠቃላይ ቀመር ተብሎ የሚታወቀው ነው

ባላ በተፈጥሮ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ግስበት ምክንያት የሚነጥሩ ኳሶች የባላ ቅርጽ ይይዛሉ
ፏፏቴወችም እንዲሁ የባላ ቅርጽ አላቸው። ምክንያቱም እንደኳሱ ግስበት ነው
  • የተተኮሰ ጥይት፣ የተወረወረ ድንጋይ፣ ሮኬቶች፣ ወዘተ.... በምድር ግስበት ምክንያት እንዲሁ የባላ ቅርጽ ይዘው ለመጓዝ ይገደዳሉ።