Jump to content

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ከውክፔዲያ
የ23:25, 12 ሜይ 2021 ዕትም (ከKZebegna (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ድርጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ሊቀ መንበር አቶ አዲሱ ለገሰ
ዋና አስፈጻሚ ባለ ሥልጣን አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም
ማእከላዊ ጣቢያ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ
የሠራትኞች ብዛት 6, 559 (ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም [2012 እ.ኤ.አ])
የመንገደኞች ብዛት (በዓመት) 5,225,000 (ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም [2013 እ.ኤ.አ])
የመንገደኛ አውሮፕላኖች 10 ቦይንግ 787 ድሪምላይነር ፣ 2 ቦይንግ 777-300ER ፣ 6 ቦይንግ 777-200LR ፣ 10 ቦይንግ 767-300ER ; 4 ቦይንግ 757-200፤ 8 ቦይንግ 737-700NG፤ 11 ቦይንግ 737-800 W፤ 17 Q400 NextGen
የጭነት አውሮፕላኖች 2 ቦይንግ 757-260F፤ 1 ቦይንግ 737-400F፤ 2 MD-11F፤ 4 ቦይንግ 777-200LRF፤
ድረ ገጽ http://www.ethiopianairlines.com


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አየር መንገድ ድርጅት ነው። አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ ወርልድ ኤይርዌይስ/ Transworld Airways (TWA) ጋር በጋራ የተመሠረተ ሲሆን አስተዳደሩ በአሜሪካኖች እጅ ነበር፤ ድርጅቱ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ተመሥርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ከአዲስ አበባ ተነሥቶ ካይሮ ድረስ አከናወነ።

አየር መንገዱ ሲመሠረት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት ዲ.ሲ. ፫ (DC 3-C47) አውሮፕላኖች ነበሩት። በዓለም ዙሪያ በአፍሪካ፤ በእስያ፤ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ክፍለ አህጉራት ወደ ፶ የመንገደኛና የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ፤ በሀገር ውስጥ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ፲፮ መድረሻዎችን ያገለግላል። ዋና የጣቢያው ማዕከል በአዲስ አበባ የሚገኘው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ልጆችንም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን እስከ አርባ ዓመት ልምድ አለው። እንዲሁም ለብዙ የአፍሪካ ሀገር ብሔራዊ አየር መንገዶችና የግል አውሮፕላኖች የጥገና አገልግሎት ይሰጣል።

አየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የተያዘ የኢትዮጵያውያን ሀብት ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ለሽያጭ እና ለግዢ እንዲሁም ለብድር አመቺ እንዲሆን ተብሎ በአየር መንገዱ ሙሉ ቁጥጥር ሥር በኬይማን ደሴቶች የተመሠረተ ድርጅት ባለቤት ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለመንገደኞች አገልግሎት አዲሱንና ዘመናዊውን የቦይንግ ፯፻፹፯ (Boeing 787) ድሪምላይነር አውሮፕላን በማዘዝና ጥቅም ላይ በማዋል ከአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሊሆን ነው። የታዘዙትን አሥር ቦይንግ ፯፻፹፯ ድሪምላይነር (Boeing 787 Dreamliner) አውሮፕላኖች እ.አ.አ. በ2009 መጨረሻ ላይ እንደሚረከብና ጥቅም ላይ እንደሚያውል ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ አየር መንገዱ 8 ቕ400 አውሮፕላኖች ከቦምባርዲየር (Bombardier ለሀገር ውስጥ መንገደኞት አገልግሎት አዟል።

፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ዓለማየሁ በቀለ በላይነህ፣ ማትያስ ሰሎሞን በላይ እና ሱልጣን አሊ ሁሴን የተባሉ ሦስት ኢትዮጵያውያን፣ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በናይሮቢ በኩል ወደ ቦምቤይ በረራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በረራ ቁ. ፱፻፷፩ በዓየር ላይ ጠለፉ። በጠላፊዎቹም ትእዛዝ ወደ አውስትራሊያ ሲያመራ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት በረራው በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ወደምትገኘው የቆሞሮስ ደሴት ተጠግቶ ከደሴቷ ግማሽ ኪሎሜትር ውቅያኖሱ ላይ ሊያርፍ ሲሞክር የዓየር ተሽከርካሪው ተሰባብሮ ፈነዳ። ከመንገደኖቹም ውስጥ፣ ጠላፊዎቹን ጨምሮ መቶ ሃያ ሦሥት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ከሞቱት መንገደኞች አንዱ፣ ኬንያዊው የፎቶ-ጋዜጠኛ ሞሐመድ አሚን ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፬፻፱ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ከቤይሩት በተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ አደጋ ምክንያት በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ውድቆ የሰመጠ በረራ ነበር።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Ethiopian Airlines የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።