ዋራድ-ሲን
Appearance
ዋራድ-ሲን ከ1745-1734 ዓክልበ. ድረስ የላርሳ ንጉሥ ነበረ። አባቱ ኤላማዊው/አሞራዊ አለቃ ኩዱር-ማቡግ በላርሳ ዙፋን ላይ እንዳኖረው ይታመናል። [1] [2] [3]
ከዘመኑ የነገሠው 12 ዓመት ሁሉ በስም ይታወቃል። በ2ኛው አመቱ፣ የካዛሉን ግድግዳ እንዳጠፋው፣ የሙቲባልንም ሠራዊት ድል አንዳደረገው ዘገበ። ከዋራድ-ሲን በኋላ ወንድሙ ሪም-ሲን ነገሠ።
ቀዳሚው ሲሊ-አዳድ |
የላርሳ ንጉሥ 1745-1734 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሪም-ሲን |
- ^ [1] Archived ማርች 6, 2009 at the Wayback Machine The Rulers of Larsa, M. Fitzgerald, Yale University Dissertation, 2002
- ^ Larsa Year Names, Marcel Segrist, Andrews University Press, 1990, ISBN 0-943872-54-5
- ^ Chronology of the Larsa Dynasty, E.M. Grice , C.E. Keiser, M. Jastrow, AMS Press, 1979, ISBN 0-404-60274-6