Jump to content

ዴቪድ ዉዳርድ

ከውክፔዲያ
(ከDavid Woodard የተዛወረ)
ዴቪድ ውድዋርድ
የትውልድ ቦታ ሳንታ ፓርባራ, ካሊፎርኒያ
የልደት ቀን ኤፕሪል 6, 1964 እ.ኤ.አ.


ዴቪድ ጄምስ ውድዋርድ (እንግሊዝኛDavid James Woodard, /ˈwʊdɑːrd/; ልደት ኤፕሪል 6፣ 1964) አሜሪካዊ ፀሐፊና ኮንዳክተር ነው፡፡ በ1990ዎቹ የፕሪኪየም የሚባለውን ቃል ፈጠረ፣ ይህ የመግቢያና የሬኪየም መዚቃ ስብጥር ነው፣ ይህም በነበረበት የቡዲዝም ዕምነት ልምድ መሰረት ከሟች ህልፈት በኋላ ወዲያው ወይም በቅርበተ-ህልፈት ወቅት የሚጫወት ሙዚቃ ነው፡፡[1][2]ሎሳንጅለስ

ውድዋርድ በኮንዳክተርነትና በሙዚቃ ዳይሬክተርናት የነበረበት የሎሳንጅለስ መታሰቢያ አገልግሎት በ2001 አሁን ላይ ስራ ባቆመው ኤንጅልስ ፍላይት በተሰኘው ጥምዝምዝ የባቡር ሀዲድ ላይ የአደጋ ሰለባዎች የሆኑትን ሟች ሊዎን ፕራፖርት እና የተጎዳች ባለቤቱን ሎላን ላምስታወስ የተደረገውን የ2001 የሙዚቃ ዝግጅት ይጨምራል፡፡[3][4] የዱር እንስሳት ወደ ታች ወርደው በተከሰከሱበት የማህር ዳርቻ አካባቢ የተደረገውን የካሊፎርኒያን ብራውን ፌሊካን ዝግጅት ጨምሮ በርካታ ሬኪየሞች ኮንዳክት አድርጓል፡፡[5]

ውድዋርድ የድሪም ማሽንን ተመሳሳይ በመስራቱ ይታወቃል፣ ይህ በመጠኑ ሳይኮአክቲቭ የሆነ አምፖል ነው፣ ይህም በዓለም ዙሪያ ባሉ የጥበብ ማዕከሎች ለህዝብ ዕይታ ቀርቧል፡፡ በጀርመን እና በኔፓል በዴር ፍሬውንድ ጋዜጣ ላይ በሚጽፋቸው ጽሑፎች ይተታወቃል፣ ጽሑፎቹ በኢንተር-ስፒሲስ ካርማ እና በዕጽዋት ንቃተ-ህሊና እንዲሁም ኒዩቫ ጀርመኒያ የተሰኘውን የፓራጓዮች መስፈር ዙሪያ የተጻፉ ናቸው፡፡[6]

ውድዋርድ የተማረው ሴይንት ባርባራ በሚገኙት ዘ ኒው ስኩል ፎር ሶሻል ሪሰርች እና ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በተሰኙ የትምህርት ተቋማት ነው፡፡[7]

ኒዩቫ ጀርመኒያ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ 2003 ውድዋርድ በጁኒፐር ሂልስ (ሎሳንጅለስ ግዛት) ካሊፎርኒያ ውስጥ አማካሪ ሆነ፡፡ በዚህ ስራ እያለ ከፕራግ ከተማ ኒዩቫ ጀርመኒያ ጋር የእህትማማችነት ግንኙነት ሀሳብ አቀረበ፡፡ ሀሳቡንም ለማሳካት ወደ ኤረስትዋይል/ሴት ዘመሟ መቀመጫ በመጓዝ ከከተማው አስተዳደሮች ጋረ ተወያይቷል፡፡ የመጀመሪያውን ጉብኝት ተከትሎ ለወዳጅነቱ ተጨማሪ ግፊት ሳያደርግ ቢቀርም ከማህረሰቡ ለሚቀጥሉት የጽሑፍ ስራዎቹ የሚጠቅሙ ጉዳዮች አግኝቷል፡፡ ለግምታዊ አቃጁ ሪቻርድ ቫግነር እና ከባሏ በርናርድ ፎርስተር ጋር በፈጠሩት ግዛት ከ1886 እስከ 1889 የኖረችው ኤልሳቤጥ ፎርስተር ኒቼ ፕሮቶ-ትራንሹማኒስት ሀሳቦች የተለየ ግምት አለው፡፡[7] ሪቻርድ ቫግነር

ድሪም ማሽን ጋር ፣ በ 1997 ገደማ

ከ 2004 እስከ 2006 ውድዋርድ ብዙ ጉዞዎችን ወደ ኒዩቫ ጀርመኒያ መርቷል፣ ይህን በማድረጉም በወቅቱ ከነበሩት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ድጋፍ አግኝቷል፡፡[8] በ 2011 ውድዋርድ ለስዊዙ ደራሲ ክርስቲያን ራችት በመካከላቸው ስለነበረው በአብዛኛው በኒዩቫ ጀርመኒያ[9] ዘሪያ የተደረገ መጻጻፍ በሁለት መድብል በሀኖቨር ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ዌርሃም ቬርለላግ እንዲታተም ፈቃድ ሰጥቷል፡፡[10] በነበራቸው የደብዳቤ ልውውጥ ውስጥ ፍራንክፈርተር አለጌሚኒ ዜቱን እንዲህ ይላል፣ "[ውድዋርድ እና ራችት] በህይወትና በጥበብ መካከል ያለውን ድንበር አጥፉ፡፡"[11] የመጀመሪያው መድብል፣ አምስት ዓመት፣ ዕትም 1[12] ኢምፔሪየም ለተሰኘው ቀጣይ የራችት ድርሰት "መዘጋጃ መንፈሳዊ ስራ " ነው ሲል ደር ስፓይግል ግምቱን ያስቀምጣል፡፡[13]

እንደ አንዲሪው ማክካን፣ "ራችት ከድዋርድ ጋር ከውድመት ወደ ተረፈውና የመጀመሪያዎቹ ሰፋሪዎች ቀጣይ ተውልድ በወረደ የአኗኗር ሁኔታ [ስር] ወደሚኖሩበት ስፍራ ተጉዟል፡፡ ጋዜጠኛው እንደሚያጋልጠው፣ ወድዋርድ ስለማህበረሰቡ የማወቅ ፍላጎት እንዲያዳብርና በአንድ ወቅት የኤልሳቤጥ ፍርስተር ኒቼ ቤተሰቦች መኖሪያ በነበረው ስፍራ ባይሬውዝ የተሰኘውን መዘውተርያ ኦፔራሃውስ እንዲገነባ አስገዳጅ ሁኔታ ፈጥሮበታል፡፡"[14][ማ 1] በቅርብ ዓመታት ኒዩቫ ጀርመኒያ መኝታ፣ ቁርስና ማረፊያ ሆኖ ወደ ተወዳጅ መዘውተሪያ ስፍራነት ተቀይሯል፡፡

ከ 1989 እስከ 2007 ውድዋርድ በብራይን ጋይሲን እና አያያ ሶቨርቪል የተበጀውን ከመዳብ ወይም ከወረቀት የተሰራ የተቀደደ ስሊንደር የያዘና በኤሌክትሪክ አምፖል ዙሪያ የሚሽከረከር ዓይን ተጨፍኖ ሲደመጥ የመድሃኒት ስካር ተጽዕኖ ወይም የህልም ስሜት ውስጥ የሚከት የድሪም ማሽን ተመሳሳይ የስትሮቦስኮፒክ ኮንትሮቫንስ ፈጠረ፡፡[15][ማ 2]

ለዊሊያም ኤስ. ቦሮውስ የ1996[16] ኤል ኤ ሲ ኤም ኤ ዕይታዊ የጀርባ ማስገቢያዎች ድሪም ማሽን ካበረከተ በኋላ ውድዋርድ ከጸፊው ጋር በመወዳጀት ለ83ኛ ዓመት ልደቱ “ቦሄሚናል ሞዴል” (ወረቀት) ድሪም ማሽን ስጦታ አበርክቶለታል፡፡[17][18] ሶዝቢ የመጀመሪያውን ማሽን በ2002 ለግል ሰብሳቢ በጨረታ ሸጧል፣ የመጨረሻው በተራዘመ ውሰተት ከቦሮው ተወስዶ በስፔንሰር የጥበብ ሙዚየም ይገኛል፡፡[19]

ማጣቀሻዎችና ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ የስዊስ ክላሲካል የቋንቋ አጥኚ ቶማስ ሽሚት የወድዋርድን የተረክ ድምጽ ከቶማስ ፓየቸን ድርሰት የጀረባ ገጸ-ባህሪ ጋር ያመሳስለዋል፡፡
  2. ^ በ1990 ውድዋርድ ልበ-ወለዳዊ የሳይኮአክቲቭ መሳሪያ የሆነውን ውጤቱ ከድሪም ማሽን ተቃራኒ የሆነውን ፌራሊሚናል ሊካንትሮፓይዘር ፈጠረ፡፡
  1. ^ ካርፔንተር፣ ኤስ. ፣ "In Concert at a Killer's Death", ሎሳንጅለስ፣ ሜይ 9፣ 2001፡፡
  2. ^ ራፒንግ፣ ኤ.፣ ውድዋርድ ምስል (ሲያትል: ጌቲ ኢሜጅስ፣ 2001)፡፡
  3. ^ ሬች፣ ኬ.፣ "Family to Sue City, Firms Over Angels Flight Death", ሎሳንጅለስ ታይምስ፣ ማርች 16፣ 2001፡፡
  4. ^ ዳውሰን፣ ጄ.፣ የሎሳንጅለስ ኤልጅልስ በረራ (ማውንት ፐልዛንት፣ ኤስ ሲ: አርካዲያ ማተሚያ፣ 2008)፣ ገጽ. 125፡፡
  5. ^ ማንዘር፣ ቲ.፣ "Pelican's Goodbye is a Sad Song"፣ ፕሬስ ቴሌግራም፣ ኦክቶበር 2፣ 1998፡፡
  6. ^ ካሮዚ፣ አይ.፣ "La storia di Nueva Germania", አይ1 ፖስት, ኦክቶበር 13፣ 2011፡፡
  7. ^ ሪኒከር፣ ሲ.፣ "Autorschaftsinszenierung und Diskursstörungen in Five Years", በጄ ቦልተን ወ ዘ ተ., አርታኢዎች, ጀርመን መኒተር 79 (ለይድን: ብሪል፣ 2016)፡፡
  8. ^ ኤፕስታይን፣ ጄ.፣ "Rebuilding a Home in the Jungle"ሳንፍራንሲስኮ ክሮኒክለ፣ ማርች 13፣ 2005፡፡ Archived ኦክቶበር 9, 2016፡፡
  9. ^ ሽሮተር፣ ጄ.፣ "Interpretive Problems with Author, Self-Fashioning and Narrator"፣ በባይርክ፣ ኮፕ፣ አርታኢዎች, ጸሐፊና ተራኪ (በርሊን: ደ ግሩይተር, 2015), ገጽ. 113–138፡፡
  10. ^ ውድዋርድ፣ ዲ.፣ "In Media Res", 032c, የበጋ 2011, ገጽ. 180–189፡፡
  11. ^ ሊንክ, ኤም.፣ "Wie der Gin zum Tonic", ፍራንክፈርተር አልጄሚኒ ዚቱንግ፣ ኖቬምበር 9፣ 2011፡፡
  12. ^ ራችት፣ ሲ.፣ እና ውድዋርድ፣ Five Years (ሃኖቨር: ዌራህን ቬርላግ፣ 2011)፡፡
  13. ^ ዳይዝ፣ ጂ.፣ "Die Methode Kracht"ዴር ስፒግል፣ ፌብሩዋሪ 13፣ 2012፡፡
  14. ^ ማክካን፣ ኤ. ኤል.፣ "Allegory and the German (Half) Century" Archived ኦክቶበር 9, 2016 at the Wayback Machineሲድኒ የመጽሐፎች ዳሰሳ፣ ነሐሴ 28፣ 2015፡፡
  15. ^ አለን፣ ኤም.፣ "Décor by Timothy Leary"ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ጃኑዋሪ 20፣ 2005፡፡
  16. ^ ናይት ሲ.፣ "The Art of Randomness"ሎሳንጅለስ ታይምስስ፣ ኦገስት 1፣ 1996፡፡
  17. ^ ዩ ኤስ ኤምባስ ፕራግ፣ "Literární večer s diskusí", ኦክቶበር 2014፡፡
  18. ^ ውድዋርድ፣ "Burroughs und der Steinbock", ሽዌይዘር ሞናት፣ ማርች 2014, ገጽ. 23፡፡
  19. ^ ስፔንሰር የጥበብ ሙዚየም፣ ድሪም ማሽን፣ ካንሳስ ዩኒቨርሲቲ፡፡

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ውድዋርድ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።