ከ«ሰርጌይ ብሪን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
ጥ robot Adding: az:Sergey Brin |
ጥ robot Adding: kn:ಸೆರ್ಗೆ ಬ್ರಿನ್ |
||
መስመር፡ 31፦ | መስመር፡ 31፦ | ||
[[it:Sergej Mikhailovič Brin]] |
[[it:Sergej Mikhailovič Brin]] |
||
[[ja:セルゲイ・ブリン]] |
[[ja:セルゲイ・ブリン]] |
||
[[kn:ಸೆರ್ಗೆ ಬ್ರಿನ್]] |
|||
[[ko:세르게이 브린]] |
[[ko:세르게이 브린]] |
||
[[ml:സെര്ജി ബ്രിന്]] |
[[ml:സെര്ജി ബ്രിന്]] |
እትም በ20:23, 27 ጃንዩዌሪ 2009
ሰርጂ ሚካይሎቪች ብሪን (እንግሊዘኛ: Sergey Mikhailovich Brin፤ ሩስኛ: Сергей (/ሰርገይ/) Михайлович Брин) (ኦገስት 21, 1973 እ.ኤ.አ. ተወለደ) ሩሲያዊ-አሜሪካዊ ሲሆን ጉግልን በመፍጠሩ ይታወቃል።
በሩሲያ የተወለደ ሲሆን፥ ብሪን ከላሪ ፔጅ ጋር ጉግልን ከመጀመሩ በፊት ኮምፒዩተር ሳይንስና ሒሳብ አጥንቷል። ብሪን ባሁኑ ጊዜ የጉግል ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት በመሆኑ ወደ 14.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አለው። ይህም ከዓለም 26ኛ እና ከአሜሪካ 12ኛው ሀብታም ሰው ያደርገዋል።
የመጀመሪያ ዓመታት
ስርጂ በሞስኮ፣ ሩሲያ ለየይሁዳ ቤተሰብ ተወለደ። 6 ዓመቱ ሲሆን ሰርጂና ቤተሰቡ ወደ አሜሪካ መጡ። አባቱ ሚካኤል በሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ማቲማቲሻን ሆኖ እስክ ዛሬ ድረስ ያስተምራል። የስርጂ እናት ዩጂኒያ ብሪን ማቲማቲሻንና ሲቭል ኢንጅነር ሆና ለናሳ ትሰራለች። ሳሙኤል የሚባል ታናሽ ወንድምም አለው።
ሰርጂ በኮምፒዩተር ዕድገት ጊዜ በማደጉ የኮምፒዩተር ፍላጎቱ ከልጅነቱ ነው የጀመረው። መጀመሪያው ያገኘው ኮምፒዩተር አንድ ኮሞዶር 64 ሲሆን ይህንንም ከአባቱ ዘጠነኛው ልደት በዓሉ ላይ ነው ያገኘው። በሒሳብና ኮምፒዩተር ያለውን ተስዕጦም ገና ትንሸ እያለ ነው ያሳየው።
ትምህርት
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በፔንት ብራንች ሞንቴሶሪ ትምህርት ቤት የወሰደ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በኤላኖር ሩዝቬልት ትምህርት ቤት አጠናቋል። ቤተስቡም የሒሳብ ዕውቀቱንና ሩሲያኛው በማዳበር ረድተውቷል። በሴፕቴምብር 1990 እ.ኤ.አ.፣ ሰርጂ ሒሳብና ኮምፒዩተር ሳይንስ ለማጥናት ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ፣ ኮሌጅ ፓርክ ገባ። በሜይ 1993 እ.ኤ.አ. የባችለር ሳይንስ ካማግኘቱ በኅላ በስኮላርሺፕ ኮምፒዩተር ሳይንስን ለማጥናት ወደ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሄደ። ከዛም ከታሰበው ጊዜ በፊት በኦገስት 1995 እ.ኤ.አ. የማስተርስ ዲግሪውን ተቀበለ። ባሁኑ ጊዜ ግን የፒ.ኤች.ዲ. ጥናቱን ላልተወስነ ጊዜ አቋርጦ ጉግል ውስጥ እየሰራ ይገኛል።