Jump to content

መነን አስፋው

ከውክፔዲያ

==

እቴጌ መነን አስፋው
ባለቤት ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ
ልጆች ልዕልት ተናኘወርቅ
ዓፄ አምኃ ሥላሴ
ልዕልት ዘነበወርቅ
ልዕልት ፀሐይ
ልዑል መኮንን
ልዑል ሣህለ ሥላሴ
ሙሉ ስም ወለተ ጊዮርጊስ (የክርስትና ስም)
አባት አስፋው፣ የአምባሰል ጃንጥራር
እናት ወይዘሮ ስኂን ሚካኤል
የተወለዱት መጋቢት ፲፯ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ.ም.
የሞቱት የካቲት ፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም.
የተቀበሩት መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

==

እቴጌ መነን አስፋውቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባለቤት ነበሩ። ግርማዊ እቴጌ መነን መጋቢት 25 ቀን 1883 ዓም በወሎ ጠ/ግዛት በአምባሰል አውራጃ ልዩ ስሙ ዕጓ ከተባለው ቀበሌ ከጃንጥራር አስፋውና ከወ/ሮ ስሂን ሚከኤል ተወለዱ። እቴጌ መነን በልጅነት ዘመናቸው በእናት በእባታው ቤት መምሀር ተቀጥሮላቸው ኣማርኛ ማንበብና መፃፍ ጠንቅቀው አወቁ። በተጓዳኝ ልዩ ልዩ የቤት ባልትና ሙያዎችን ተምረው በማጠናቀቃቸው የቤት ራስ ለመባል በቅተዋል።

መነን የሚለው ቃል በዐማርኛ የሴት ልጅ ስም ሲሆን ታላቁ ምሁር ዓለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ ቀጭን ፈታይ፣ ባለሟያ፤ ወይም መልከ መልካም፤ ትክክል ፍጽምት ሕጸጽ የሌለባት ማለት እንደሆነ አፍታትተው አሥፍረውታል።[1]

  1. ^ "መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሓዲስ" (፲፱፻፵፰ ዓ/ም)፣ ገጽ ፮፻