ሸክላ፣ የአፈር ውጤት ነው። የሸክላ ውጤቶች ፥የቤት ቁሳቁሶችን፣ እንደ ድስት፣ ገንቦ፣ ማሰሮ፣ ሰሀን፣ ኩባያ ወዘተ እንዲሁም ለግንባታ ፥ቤት፣ ግቢ አጥር የመሬት ምንጣፍ ወለሎችን ወዘተ ፤የተለያዩ ጌጣጌጦችን ቅርፃቅርፆችን ወዘተ የሚሰራበትና የሰው ልጅ ሥልጣኔ ከጀመረበት ጀምሮ እስከአሁን ያልተለየው የዕደጥበብ መሠረት ነው።