Jump to content

አርተር ሾፐናውር

ከውክፔዲያ
አርተር ሾፐናውር

አርተር ሾፐናውር (የካቲት ፲፮ ቀን ፲፯፻፹ – መስከረም ፲፪ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.) ጀርመናዊ ፈላስፋ ነበር።

በሾፐናውር እምነት የማናቸው ነገሮች ምንነት (ኢሴንስ) ፣ ሰዎችንም ጨምሮ፣ እውቀታቸው፣ ምክንያታዊነታቸው ወይምን መንፈሳቸው ሳይሆን ፈቃዳቸው ነው ይል ነበር። ፈቃድሲል ማናቸውንም ነገሮች፣ ከአለቶች ጀምሮ እስከ ሰው ልጅ ኅልው እንዲሆኑ የሚገፋቸውን ጉልበት ነው። ይህ ጉልበት ምንም ምክንያት የለውም፣ ኅልው ለመሆኑም ምክንያት የለውም፣ ስለሆነም የሰው ልጅ ስቃይ ከዚህ ምክንያት የለሽ እውር ጉልበት ይመነጫል ብሎ ሾፐናውር ያስተምር ነበር።

«የሰው ልጅ የሚፈልገውን ማድረግ ይችላል
ነገር ግን የሚፈልገውን መፈለግ አይችልም»

ሾፐናውር

ሾፐናውር ለዚህ ስቃይ ማስታገሻ ይሆናል ብሎ የዘየደው ፈውስ ሰወች የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዲኖራቸው መምከር ነበር። የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዴት ይገኛል ለሚለው የእርሱ መልስ የሰው ልጅ ፍላጎቱን ማሟላትን እንዲክድ፣ ጊዜ ሰውቶ እራሱን እንዲመረምርና ምን ቢሰራ ስቃዩን እንደሚያመልጥ በማሰብ ነው። ለስቃዩ ማምለጫ ከአዘዘው ውስጥ የኪነት ስራወችን መስራትና የተሰሩትን ማድነቅ፣ በተለይ ሙዚቃን ያጠቅሳል። ሙዚቃ፣ በሾፐናውር አስተሳሰብ፣ ለሰው ልጆች ኅልው መሆን (መኖር) አንዱ ምክንያት ነው።

ሾፐናውር ለሪቻርድ ዋግነርፍሬደሪክ ኒሺሉድዊግ ዋይንስታይንሲግመንድ ፍሮይድሊዮ ቶልስቶይካርል ጀንግ እና ሌሎች ብዙ የምዕራቡ አለም የኪነትና ፈጠራ ሰወች ላይ ተፅዕኖ ያሳደረ ፈላስፋ ነበር።

  • "እያንዳንዱ ሰው የራሱን የዕይታ ወሰን እንደ የአለም ወሰን አድርጎ ይቆጥራል"
  • "በአጠቃላም መክሉ፣ የየዘመኑ ጠቢባን አንድ አይነት ነገር ተናግረዋል፣ የየዘመኑ ጅሎች በአንጻሩ የተነገረውን ተቃራኒ አድርገዋል፣ በዚህ አይነት መንገድ መጭው አለምም ይቀጥላል"
  • "ጋብቻ ማለት የራስን መብት መግመስና ግዴታ በሁለት እጥፍ ማሳደግ ነው"
  • "የሰው ልጅ ደስታ ሁለት ጠላቶች አሉት፡ ህመምና ድብርት"
  • "ችሎታ ማንም ሰው መምታት ያቃተውን ኢላማ ይመታል፣ ጥበብ ግን ማንም ሰው ያላየውን ኢላማ ይመታል"