Jump to content

ፍሮይድ

ከውክፔዲያ
(ከሲግመንድ ፍሮይድ የተዛወረ)
ሲግመንድ ፍሮይድ

ሲግመንድ ፍሮይድ (1856 - 1939 እ.ኤ.አ.) ኦስትሪያ የተወለደ የነርቭ ሃኪም እና ስነ ልቡና ተመራማሪ ነበር። የትንተናዊ ስነ ልቡና ( የሳይኮአናሊሲስ ) አባት እየተባለ ይጠቀሳል።

ፍርይድ በስነ ልቡና ጥናት ታዋቂ የሆነው የሰውን ልጅ ያልነቃ ኅሊና በሳይንሳዊ ዘዴ በማጥናቱ ነበር። እያንዳንዱ ግለሰብ የነቃ ኅሊና እንዳለው ሁሉ ያልነቃም ህሊና አለው፣ ሆኖም ግን ግለስቦች ያልነቃውን የአዕምሮ ክፍል ምን እንደሚያሳብ ማወቅ አይችሉም፡ በተጨማሪ ግለሰቦች ይህን የአዕምሮ ክፍላቸውን ማዘዝም ሆነ መቆጣጠር አይችሉም። ያልነቃው ክፍል በራሱ ፍላጎት ግለሰቡ በኅይወት እስካለበት ዘመን ድረስ ያስባል።

ይህን ሃሳብ በጽሁፍ ባቀረበበት ወቅት ፍሮይድ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሷል፡ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች እራሳቸው የማያውቁትና የማይቆጣጠሩት ክፍል አዕምሮአቸው ውስጥ እንዳለ ለመቀበል ስላቃታቸው ነበር።

በፍሮይድ አስተሳሰብ በህይወት ከመኖር ቀጥሎ ለሰው ልጅ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ፍትወተ ስጋ እንደሆነ ጽፏል። ይህን ፍላጎት ሊቢዶ በማለት ተንትኗል። የሰው ልጆች የማይፈልጉትን ሁሉ እንዲያረጉ እስከማስገደድ ድረስ ይህ ሊቢዶ ያስገድዳል ብሏል።

ፍሮይድ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታይ ስለነበር በ1930ወቹ የሱ መጽሃፎች ተሰብስበው እንዲቃጠሉ ናዚዎች አደረጉ። በ1938 እ.ኤ.አ.አዶልፍ ሂትለር ሰራዊት ፍሮይድና ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ለማድረስ እንደሚሹ ሲያረጋግጥ ፍሮይድ ከነቤተሰቦቹ ቪየና (ኦስትሪያ)ን ለቆ ወደ እንግሊዝ ተሰደደ።