Jump to content

የሥነ፡ልቡና ትምህርት

ከውክፔዲያ
(ከስነ ልቡና የተዛወረ)

ስነ ልቦና ማለት በሰው ውስጥ የሚኖር እንስሶች የሌለላቸው ነፍስ ማለት ነው። ሰው እና እንስሳት አንድ የሚያደርጋቸው ሕይወታቸው ሲሆን ህይወት ደግሞ የምትጠፋ ናት። ሰነ ልቦና ግን ከተፈጠርን ጀምሮ አብሮን የሚኖር ውስጣዊ እኛነታችን ነው።

ሙት ባሕር እስራኤል በተገኙት ብራና ጥቅሎች በአንዱ «የሥርዓት መመሪያ መጽሐፍ» በተባለ ብራና ውስጥ ለሰዎች ሁሉ ሁለት መናፍስት እንደተሾሙ ይላል፤ እነርሱም ሀሠት ወይም ትእቢት (ጥላ) እና እውነት ወይም ኅሊና (ብርሃን) ይባላሉ። ለዚህ እምነት በቤተ እስራኤል ዘንድ ተመሳሳይ ጽሁፍ አለ፤ የተሾሙ መላእክት በጐ ወይም ጥፉ አድራጎት በወርቅ ይመዝገባሉ ይላል።


ፕላቶ በጻፈው ፋይድሮስ በተባለው ጽሑፍ፣ ሶክራቴስ እንዲህ ይላል፦ «ነፍሱን እንደ ሁለት ባለ ክንፍ ፈረሶችና የሠረገላ ነጂ እናስመስላለን። ... የሰብዓዊ ነፍስ ነጂ ሁለቱን ይነዳል፤ ከፈረሶቹ አንዱ መልካምና ከመልካም ዘር ነው፣ ሌላው ግን በባኅርይም ሆነ በዘር እጅግ ተቃራኒ ነው። ስለዚህ በኛ በኩል መንዳቱ በግድ ከባድና አስቸጋሪ ነው።»

በዘመናዊው ሥነ ልቡና ደግሞ አእምሮ በሁለት ክፍሎች ይለያል። አንዱ ክፍል በደረታቸው የሚስቡ እንስሳት ባይኖራቸው የሚጠቡ እንስሶች ብቻ ይዘውት ነው። ሌላው ክፍል ለእንስሳት ሁሉ የጋራ ነው።

የሥነ-ልቡና ጥናት መርሆዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሰው ዘር ከአብዛኛው እንስሳ ለየት የሚለው እያንዳንዱ የሚያስበው ነገር የተለያየ መሆኑ ነው። እንስሶች ያውም የአዕምሮአቸው ክብደት በጣም ዝቅተኛ የሆኑ ብቻ ናቸው አንድ ነገር ላይ አተኩረው ወይም አንዱን ተከትለው የሚሄዱት። አንዳንድ የአሳ ዘሮች፤ አንዳንድ የወፍ ዘሮች፤ በመጠኑ እንደ በግ ያሉ እንስሳዎች እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ። ሰውን በቡድን መድቦ ይሄ እንዲህ ያስባል፤ ያ እንዲያ ያስባል ማለት የሰውን ልጅ አዕምሮ ረቂቅነት አለመገንዘብ ነው።

የሥነ-ልቡና የጥናት አድማስ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የምርመራ ዘዴዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሥነ-ልቡና ጥናት ሂሶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]