Jump to content

እንጀራ

ከውክፔዲያ

እንጀራዳቦ ዓይነት ሲሆን ከጤፍ፣ ከስንዴ፣ ከገብስ፣ ከሩዝ ወይም ከበቆሎ ሊዘጋጅ ይችላል። ከቀይ ወይም ከነጭ ጤፍ የሚዘጋጀው እንጀራ ተፈላጊና ተመራጭ ነው።

አስፈላጊ

  • ጥቁር ወይም ነጭ የጤፍ ዱቄት
  • የጤፍ እርሾ
  • አመቺ ማቡኪያ
  • መጋገሪያ ምጣድ
  • የምጣድ ማሰሻ (የተወገጠ ጎመንዘር)
  • ሊጥ ማዞርያ የሚያመች እቃ
  • መሶብ እና እንጀራ ማውጫ ሰፊድ

አሰራር

  • 1. የጤፉን ዱቄት እንዳስፈላጊነቱ ቀንሶ በማቡኪያ ውስጥ ማድረግ እና እርሾውን ጨምሮ ማቡካት
  • 2. ቡኮው ውሃ እንዲያቀር ቀጠን ማድረግ ከዛም መክደንእና
  • 3. ከሶስት ቀን በኋላ ያቀረረውን እርሾ መድፋት
  • 4. እናም በድስት ለ ቡኮው በቂ የሚሆን ውሃ አፍልቶ ከ ቡኮው ቆንጥሮ እያማሰሉ መጨመር (አብሲት መጣል)

አብሲሲቱ የሊጡ 1/3 መሆን አለበት

  • 5. አብሲቱ በረድ ሲል ቡኮው ላይ መጨመር እና ቡኮው ሳይቀጥንሳይወፍር አዋህዶ ኩፍ እንዲል ከድኖ ማቆየት
  • 6. ሊጡ ኩፍ ሲል ምጣዱን ማስማት እና በመጥለቂያ እየቀነሱ መታዱላይ ማዞር (መጋገር )
  • 7. አክንባሎ ወይም የምጣዱን ክዳን መክደን እና ትንሽ ቆይቶ እንጀራውን ማውጣት