Jump to content

ዝግመተ ለውጥ

ከውክፔዲያ
፫ቱን የሕይወት ዓይነቶች እሚያሳይ ምስል

የአንድ ሕይወት ያለው ማህብረሰብ የዘር ውርስ ባህሪይ ከትውልድ ወደትውልድ እየተቀየረ መሄዱ ዝግመተ ለውጥ ይባላል። ቻርለስ ዳርዊን ይህን ኩነት በማስተዋልና በሳይንሳዊ አመክንዮ አሰደግፎ በመተንተኑ የመጀመሪያው ሰው ነው። ዳርዊን በተጨማሪ የተፈጥሮ ምርጫ ባለው ኅልዮቱ ሕይወት ያላቸው ማህበረሰቦች ዝግመተ ለውጥ እሚያካሂዱት ምንም እንኳ በዘፈቀደ ስህተት እየፈጸሙ ቢሆንም፣ ተፈጥሮ እራሷ በምትፈጥረው መሰናክሎች እኒህን መሰናክሎች አልፈው የሚሄዱትን በመምረጧ ነው። ዳርዊን የተፈጥሮ ምርጫን አስተሳሰብ ከ፫ የሚታዩ ነገሮች አንጥሮ ነበር ያወጣው፦ ፩) እንስሳትም ሆነ እጽዋት ወደፊት ሊኖር ከሚችሉ ዘሮች በላይ አተረፍርፈው ነው እሚራቡት ፪) ሕይወት ያላቸው እያንዳንዳቸው ነገሮች ሁልጊዜ የተለያየ ጸባይ ነው ያላቸው፣ ስለሆነም እያንዳንዳንቸው በቀጣይ የመኖር ዕድላቸው የተለያየ ነው ፫) ስለሆነም የአንድ ማህበረሰብ አባላት ሲሞቱ፣ የሚገላቸውን ነገር ጠንክረው እሚቋቋሙት ግለሰቦች ብቻ በሕይወት ቆይተው ወደፊት መራባች ይችላሉ። ስለሆነም ቀስ በቀስ እነዚህ በህይወት ያሉ፣ በህይወት የሌሉትን አይነቶች እየተኩ ይሄዳሉ።

በ፳ኛው ክፍለ ዘመን ጄኔቲክስ (ሥነ በራሂ) እና ዝግመተ ለውጥ ተዋህደው ማህበረሰባዊ ጄኔትክስ እሚባለውን ጥናት ለመፍጠር ችለዋል። አንድ ማህበርሰብ ለየት ያለ ግለሰቦችን ለመፍጠር ከሚያስችሉት መንገዶች አንዱ ሙቴሽን የተባለው ሂደት ሲሆን፣ ሙቴሽን እሚፈጠረው የዚያ ግለሰብ ዲ ኤን ኤ ከወላጆች ሲወረስ በሚደረግ ስህተት (ወይም እቅድ) ነው።

ሌሎች አስተያየቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ባለሙያ ንድፍ የተባለው ትምህርት ከሥነ በራሂ ጥናት የምንማረው መረጃ ሁሉ በፈጣሪው እቅድ እንደ ሆነ ለመግለጽ ይሞክራል። በተለይ በመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ፩፡፳፮ መሠረት በመሰለ ስሜት፣ «ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፣ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፣ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ» ይላል።

የሰው ልጅ ሐብለ በራሂ (ክሮሞሶም) ከሕያዋን ሁሉ በተለይ ለቺምፓንዚ ጦጣ ሐብለ በራሂ ዝምድና እንዳለው ተገልጿል። ቺምፓንዚ ግን እንደ ሰው ልጅ ሳይሆን ሌሎችን እንስሳት ወይም አትክልት ለማዳ ለማድረግ እንዳልተዘጋጀ ግልጽ ነው። በዝርዝሩ ስንመልክተው፣ የሰው ልጅ ሐብለ በራሂና የቺምፓንዚ ሐብለ በራሂ የሚለያዩ በአንዱ እሱም በሰዎች ፪ኛው ሐብለ በራሂ ሲሆን፣ በቺምፓንዚ ግን በዚያው ሥፍራ ሁለት ልዩ ልዩ አጫጭር ሐብለ በራሂዎች አሉዋቸው። ከዚህ መረጃ የቺምፓንዚ ሐብለ በራሂ ወደ ሰው ልጅ ሐብለ በራሂ ለመቀይር፣ እነዚህ ሁለት ልዩ ልዩ አጫጭር ሐብለ በራሂዎች አንድላይ በትክክል በፍጹምነት በጥንቃቄ በእቅድ ማጋጥምና ማዋኸድ አስፈለገ። ይህ ድርጊት ተዓምር መሆን ነበረበትና ለ«ባለምያ ንድፍ» እንደ ማስረጃ ይቆጠራል። ስለዚህ የሰው ልጅ ክሮሞሶም በአንድ ትውልድ መከሠት ነበረበት እንጂ በብዙ ሚሊዮን ዘመን ዝግታዊ ሂደት የሚለወጥ አይመስልም፤ የሰው ልጅ በራሂ አራያ ከቺምፓንዚ በራሂ አራያ የተለወጠበትም ዘመን ከ6000 ዓመታት በፊት አይሆንም ይላል።