ጥንታዊ እንግሊዝኛ
ጥንታዊ እንግሊዝኛ (Englisc /ኧንግሊሽ/) በእንግሊዝ አገር ከ440 ዓ.ም. ገደማ እስከ 1100 ዓ.ም. ያሕል የተናገረ ቋንቋ ነበር። ዛሬ ጀርመንና ዴንማርክ ከተባሉት አገሮች ፈልሰው በእንግሊዝ በተስፈሩት ሕዝብ የተናገሩበት ሲሆን የዘመናዊ እንግሊዝኛ ቀድሞ አይነት ነው። ሆኖም በቃላትም ሆነ በስዋሰው ከዘመናዊ እንግሊዝኛ በጣም ይለያል። ቅርብ ዘመዶቹ ጥንታዊ ፍሪዝኛ እና ጥንታዊ ሴክስኛ ናቸው።
ጥንታዊ እንግሊዝኛ በርካታ ተመሳሳይ ቀበሌኞች ነበሩት። በተለይ በስሜን እንግሊዝ የኖሩት የአንገሎች መነጋገርያ በደቡብ ከኖሩት ከሴክሶች ትንሽ ተለያየ።
ከ800 ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ስሜኑ በቫይኪንጎች ስለተወረረ በንጉስ አልፍሬድ ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ። ቢሆንም የቫይኪንጎች ቋንቋ ኖርስኛ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ጋር ዝምድና ነበረውና ከኖርስኛ አያሌው ቃላት ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ለምሳሌ የእንግሊዝኛ ቃላት sky /ስካይ/ (ሰማይ) leg /ለግ/ (እግር) እና they /ዘይ/ (እነሱ) የደረሱ ከኖርስኛ ነበር። በእንግሊዝ ኗሪዎች ቋንቋ (በጥንታዊ እንግሊዝኛ) እነዚህ ቃላት 'ሄዮቮን'፣ 'ሽያንካ' እና 'ሂዬ' ሆነው ነበር።
የተማሩ ሰዎች (መምህራን ወይም ቄሶች) በብዛት የሮማይስጥ ዕውቀት ስለነበራቸው ደግሞ ከሮማይስጥ ተጽእኖ አንዳንድ ቃላት የዛኔ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ንጉሥ አልፍሬድ እራሳቸው ብዙ መጻሕፍት ከሮማይስጥ አስተረጎሙ።
ኖርማኖች እንግሊዝን በ1059 ከወረሩ ጀምሮ እንግሊዝኛ ከትምህርት ቤት ስለ ተከለከለ በየጥቂቱ ባሕርዩ እጅግ ተለወጠ።
በጥንታዊ እንግሊዝኛ እያንዳንዱ ስም የተወሰነ ጾታ (ወንድ፣ ሴት ወይም ግዑዝ) ነበረው። ለምሳሌ sēo sunne /ሴዮ ሱነ/ (ፀሐይቱ) አንስታይ፣ se mōna /ሴ ሞና/ (ጨረቃው) ተባዕታይ፣ þæt wæter /ዛት ዋተር/ (ውኃው) ግዑዝ ነበር።
ቋንቋው መጀመርያ ፉሶርክ በተባለው የሩን ፊደል ሲጻፍ ክርስትና ከተቀበለ በኋላ ግን በላቲን አልፋቤት ሊጻፍ ጀመረ። አንዳንድ ተጨማሪ ፈደላት እንዲህ ነበሩ:
- ȝ - ይህ ፊደል (ከአይርላንድኛ ገብቶ) እንደ 'ይ' ወይም 'ግ' ወይም 'ኅ' ሊጠቀም ይችል ነበር።
- ð - ይህ ፊደል ከላቲን d ተቀይሮ እንደ 'ስ' ወይም 'ዝ' ሊጠቀም ይችል ነበር።
- þ - ይህ ከቀድሞው ፉሶርክ ተገኝቶ ደግሞ እንደ 'ስ' ወይም 'ዝ' ጠቀመ።
- ƿ - 'W' የሚለው ፊደል ገና ስላልኖረ 'ው' ለመጻፍ በዚህ ፊደል (ከፉሶርክ ተገኝቶ) ነበር። በኋላ ዘመን ከp (ፕ) ጋር ስላለው ተመሳሳይነት ይህ ፊደል ጠፋ። ስለዚህ የዛሬ ሊቃውንት ጥንታዊ እንግሊዝኛ የሚጽፉት በዘመናዊው 'w' ነው።
- Fæder ure þu þe eart on heofonum,
- Si þin nama gehalgod.
- To becume þin rice,
- gewurþe ðin willa, on eorðan swa swa on heofonum.
- urne gedæghwamlican hlaf syle us todæg,
- and forgyf us ure gyltas, swa swa we forgyfað urum gyltendum.
- and ne gelæd þu us on costnunge, ac alys us of yfele. soþlice.
- ፋደር፡ ኡረ፡ ዙ፡ ዘ፡ ኤየርት፡ ኦን፡ ሄዮቮነም፣
- ሲ፡ ዚን፡ ናማ፡ ይሃልጎድ።
- ቶ፡ በኩመ፡ ዚን፡ ሪቸ፣
- ይዉርሰ፡ ዚን፡ ውላ, ኦን፡ ኤዮርሳን፡ ሷ፡ ሷ፡ ኦን፡ ሄዮቮነም።
- ኡርነ፡ ይደይኋምሊቻን፡ ህላፍ፡ ሲውለ፡ ኡስ፡ ቶደይ፣
- አንድ፡ ፎርዪውፍ፡ ኡስ፡ ኡረ፡ ዪውልታስ, ሷ፡ ሷ፡ ዌ፡ ፎርዪውቫስ፡ ኡረም፡ ዪውልተንደም።
- አንድ፡ ነ፡ ይለይድ፡ ዙ፡ ኡስ፡ ኦን፡ ኮስትኑንገ, አክ፡ አሊውስ፡ ኡስ፡ ኦፍ፡ ኢውቨለ። ሶስሊቸ።
- The Electronic Introduction to Old English Archived ጁን 15, 2006 at the Wayback Machine
- First steps in Old English - a course for absolute beginners
- Old English (Anglo-Saxon) alphabet
- Bosworth and Toller, An Anglo-Saxon dictionary Archived ሜይ 9, 2008 at the Wayback Machine
- Old English - Modern English dictionary
- The Origins of Old English Archived ጃንዩዌሪ 15, 2007 at the Wayback Machine
- Shakespeare's English vs Old English
- Guide to using Old English computer characters Archived ጁን 15, 2010 at the Wayback Machine (Unicode, HTML entities, etc.)
- Dictionary of Old English Project at the University of Toronto
- The Germanic Lexicon Project
- Text Collections - Texts and Translations Archived ጃንዩዌሪ 15, 2007 at the Wayback Machine