ጥንጁት
Appearance
ጥንጁት (otostegia integrifolia) በኢትዮጵያና በየመን ብቻ የሚበቅል እጽ ሲሆን ብዙ ጥቅም አለው። ባብዛኛው ግን የመጠጥ እቃዎችን እንደ ጋን እና ገምቦ ያሉትን ለማጠን የሚያገለግል ነው።
ልብስም ለማጠን፣ በአንድም ሥነ ስርዓት እናትን በወለደችው በዐሥረኛው ቀን ለማጠን ያገልግላል።[1]
ጢሱም ለሳንባ ነቀርሳ ወይም ለማስታወክ በባህላዊ ሕክምና ተዝግቧል።[2]
የጥንጁት ቅጠል ጭማቂ በውሃ ለሆድ ቁርጠት ወይም ለመጋኛ ለማከም ሊጠጣ ይችላል።
ለትኩሳት («ምች»)፣ የጥንጁትና የዳማ ከሴ ቅጠልና አገዶች፣ እንደ ጢስ መተንፈስ ያከማል። ወይም ደግሞ የጥንጁትና የዳማ ከሴ ቅጠላና አገዶች፣ የብሳናና የነጭ ባሕር ዛፍ ቅጠል፣ እና የፌጦ ዘር በውሃ ተፈልተው እንፋሎቱን መተንፈስ ለ«ምች» ያከማል።[3]
በኮረብቶች፣ በተወ መሬት፣ በስሜን ኢትዮጵያ (በጌምድር፣ ትግራይ) ተራ ቊጥቋጥ ነው።
- ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
- ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
- ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም