ፍልስፍና
ፍልስፍና የሚለው ቃል ከግሪኩ «Philos» /ፊሎስ/ ማለትም ፍቅር እና፣ «sophos» /ሶፎስ/ (ጥበብ) የተገኘ ውሁድ ነው። በቀጥታው የጥበብ ፍቅር ወይም ፍቅረ ጥበብ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በመሆኑም ፍልስፍና እውቀትን፣ እውነትን፣ ጥበብን መውደድ፣ መሻት፣ መመርመር ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ባንድ በኩል ወደ ጥበብ የተሳበ፣ ጥበብን የወደደ እንደዚሁም የጥበብ ባለሟልን የሚያመለክት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጥበብን ወዶ ሌላውም እንዲወድ ምክንያት የሚሆን ለማለት ይውላል። ይህ የጥናት ክፍል በዋናነት ነገሮችን በመላምታዊ መንገድ ለመመርመር ይሞክራል።
የፍልስፍናን ምንነት ለማወቅ የሚጠይቃቸውን ዋነኛ ጥያቄዎች እንመልከት።
ፍልስፍና የሚመረምራችው አምስት ዋነኛ ቁምነገሮች ህላዌ፣ ግብረገብ፣ ዕውቀት፣ እውነት፣ እና ውበት ናቸው። ፈላስፋዎችን ለብዙ ዘመናት ሲያስጨንቁ ከቆዩ ጥያቄዎች ውስጥ
- እውነት ምንድር ነው? አንድን አስተያየት ለምንና እንዴት እውነት ወይም ሃሰት መሆኑን እናውቃለን? ጥበብስ ምንድር ናት?
- አዋቂነት የሚቻል ነገር ነውን? ማወቃችንን እንዴት እናውቃለን? አዋቂነት የሚቻል ነገር ከሆነ የታወቀ እና ያልታወቀ ማለት ምንድር ነው? ከታወቀው ያልታወቀውን እንዴት መሻት እንችላለን?
- ግብረገብ በሆነው እና ባልሆነው መካከል ልዩነት አለን? ካለስ ልዩነቱ ምንድር ነው? የትኞቹ ድርጊቶቻችን ናቸው ልክ? ልክ ያልሆኑትስ የትኞቹ ናቸው? ሥነምግባራዊ መስፈርቶች ቋሚ ናቸው ወይስ ተነፃፃሪ? እንዴትስ መኖን አለብኝ?
- ገሃድ የሆነው ምንድር ነው? የገሃድ ነገሮች ተፈጥሮአቸው እንዴት ያለ ነው? እውን አንዳንድ ነገሮች ከኛ ግንዛቤ ውጭ መኖር ይቻላቸዋልን?
- ውበት ምንድር ነው? ውብ የሆኑ ነገሮች ከሌሎቹ በምን ይለያሉ? ሥነጥበብ ምንድር ነች? ሃቀኛ ውበት የገኛልን? የሚሉት ናቸው።
እነዚህ ከላይ በደፈናው የተጠቀሱ ጥያቄዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው አመክንዮአዊ፣ ሥነ-እውቀታዊ፣ ሥነ-ምግባራዊ፣ ሥነ-ኃልዮአዊ፣ እና ሥነ-ውበትአዊ በመባል ይታወቃሉ። ምንም እንኳን እነዚህ ዋነኞቹ ጥያቄዎች ይሁኑ እንጂ ብቸኞቹ አይደሉም። በተጨማሪም በመካከላቸው አንዳንድ መደራረብ ይታያል። ታዋቂው የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ ሥነ-መንግሥት፣ ሥነ-ተፈጥሮ፣ ሥነ-ምድር፣ ሥነ፡ሕይወት፣ ሥነ-አየር እና ሥነ ፈለክ የፍልስፍና ክፍሎች ናቸው ብሎ ያምን ነበር።
ሌሎች የፍልስፍና ባህሎች ከምዕራባውያን ፍልስፍና በተለየ በነዚህ ጉዳዮች ላይ በዙም አላተኮሩም። ምንም እንኳን የሂንዱ ፍልስፍና በዚህ አንፃር ከምዕራባውያኑ ቢመሳሰለም እስከ 19ኛው ምዕት-አመት ድረስ በኮሪይኛ፣ በጃፓንኛ፣ እና በቻይንኛ ውስጥ "ፍልስፍና" የሚል ቃል ይገኝ አልነበረም። በተለይ የቻይና ፈላስፎች ከግሪኮቹ ለየት ያለ የምደባ ስርዓት ይከተሉ ነበር።
የምዕራቡ አለም ፍልስፍና የሚጀምረው ከግሪኮች ሲሆን የመጀመሪያው ፈላስፋ ተብሎ የሚታወቀው ታሊዝ ነው። ይህ ሰው የኖረበትን ጊዜ ለማወቅ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም። ይኸውም በ593 ዓክልበ. (ዓም) የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚኖር በመተንበዩ ከዚህ ጊዜ የተወሰነ አመት ቀደመ ብሎ ማይሌጠስ በተባለችው የትንሹ እስያ (የአሁኑ ቱርክ) ክፍል እንደተወለደ የታወቀ ነው። ታሊዝ ዓለም እና በውስጡ ያሉ ነገሮች ሁሉ ከውሃ እንደተፈጠሩ ያምን ነበረ። ከሱ በኋላ የተነሱ የግሪክ ፈላስፎች የሱኑ መንገድ በመከተል ዓለም ከአንድ ወይም ከሌላ ነገረ እንደተፈጠረች አስተምረዋል። ለምሳሌ አናክሲሜነስ የዓለም ጥንተመሰረቷ አየር ነው ሲል፣ ሄራቅሊጠስ እሳት ነው ብሏል። አናክሲማንደር ከነዚህ ሁሉ ለየት በማለት የዓለም መሰረቷ ይህ ነው የማይባል «apeiron» ወይም የትየለሌ የሆነ ነገር ነው ይላል።
የምእራቡን ዓለም ፍልስፍና እስክ 1900 ድረስ ቅርጽ እንዳስያዙ የሚነግርላቸው ፈላስፋዎች የሚከተሉት ናቸው፡
ሶቅራጥስ፣ አሪስጣጣሪስ፣ ፕላጦ፣ አክዊናስ፣ ኤራስመስ፣ ማኪአቬሌ፣ ቶማስ ሞር፣ ሞንታጝ፣ ግሮቲየስ፣ ዴካርት፣ ሆበስ፣ ስፒኖዛ፣ ሎክ፣ ሌብኒሽት፣ በርክሌ፣ ሑሜ፣ ቮልቴይ፣ ሩሶ፣ ካንት፣ ሺለር፣ ሄግል፣ ሾፐናዎር፣ ጆን ኦስቲን፣ ጄ.ኤስ. ሚል፣ ኮምቴ፣ ዳርዊን፣ ማርክስ፣ እንግልስ፣ ፍሬደሪሕ ኚሼ፣ ዱርካሂም
የምስራቁ አለም ፍልስፍና መነሻ ኢትዮጲያ ናት፡፡እንደውም የመላው አለም፡፡ በተለይ ኮከባቸው gemini የሆኑት የሐበሻ ተወላጆች የኮከባቸውን ሀያልነት በመጠቀም ወደ አረቡ አለም በመገስገስ የምድራችንን የፍልስፍና መንገድ ቀይሠዋል፡፡[ዋቢ መጻሕፍት ያስፈልገዋል]
“ሐኪም” حَكِيم ማለት “ጥበበኛ” ማለት ሲሆን “ሓኪም” حَٰكِمِين ማለት ደግሞ “ፈራጅ” ማለት ነው፤ ሁለቱም “ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” “ተጠበበ” ከሚል ግስ የመጡ ናቸው፤ “ሒክማህ” حِكْمَة ማለት “ጥበብ” ማለት ሲሆን “ሑክም” حُكْم ደግሞ “ፍርድ” ማለት ነው፤ ጥበብ እና ፍርድ የጥበበኛው እና የፈራጁ አላህ ባህርያት ናቸው፤ አላህ እጅግ በጣም ጥበበኛ ነው፦ 28፥9 «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው *ጥበበኛው* አላህ ነኝ፡፡ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّهُۥٓ أَنَا ٱللَّهُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ 3፥6 እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው *ጥበበኛው* ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى يُصَوِّرُكُمْ فِى ٱلْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَآءُ ۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብን ከአላህ የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጦታል፦ 2፥269 *ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብንም የሚሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ*፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡ يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
አላህ ጥበብን ለሰው ልጆች በዐቅል እና በነቅል ይሰጣል፤ እነዚህ ሁለት የጥበብ ጭብጦችን ነጥብ በነጥብ እንይ፦
ነጥብ አንድ
- “ዐቅል”
“ዐቅል” عقل ማለት “ግንዛቤ”Metacognition” ማለት ሲሆን አላህ በቁርአን “ለዐለኩም ተዕቂሉን” لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُون ይለናል፦ 12:2 በእርግጥ እኛ *ትገነዘቡ ዘንድ* ዐረብኛ ቁርአን ሲሆን አወረድነው። إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ 2:242 እንደዚሁ አላህ አንቀጾቹን *ትገነዘቡ ዘንድ* ለእናንተ ያብራራላችኋል፡፡ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
“ትገነዘቡ ዘንድ” የሚለው ቃላት በአጽንዖትና በእንክሮት ልናጤነው የሚገባ ሃይለ ቃል ነው፤ የሰው ልጅ “አዕምሮ” እራሱ “ዐቅል” ይባላል፤ ዐቅል የጥበብ ተውህቦ”faculty” ነው፤ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ጥበብን ይወዳል፤ “ፊሎሶፍይ” φιλοσοφία የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ፊሎስ” φίλος “ፍቅር” እና “ሶፎስ” σοφός “ጥበብ” ሲሆን “የጥበብ ፍቅር” ማለት ነው፤ ይህም ሥነ ጥበብ በውስጡ፦
- ሥነ-አመክንዮ ”logic”፣
- ሥነ-ኑባሬ ”Ontology”፣
- ሥነ-እውነት ”metaphysics”፣
- ሥነ-ዕውቀት ”epistemology”፣
- ሥነ-መለኮት ”theology”፣
- ሥነ-ምግባር ”ethics”፣
- ሥነ-ውበት ”esthetics”፣
- ሥነ-መንግሥት ”politics”፣
- ሥነ-ቋንቋ ”Linguistics”
የመሳሰሉት እሳቦት ይዟል። ጥበብ”craft” እራሱ፦ ሥነ-ጥበብ፣ እደ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ እና አውደ-ጥበብ ለአሉታዊ ነገር ከተጠቀሙበት ምግባረ-እኩይ”witch-craft” ሲሆን በአውንታዊ ከተጠቀምንበት ምግባረ-ስናይ”art-craft” መማሪያም ነው፤ አላህ፦ “አፈላ ተዕቂሉን” أَفَلَا تَعْقِلُون ይለናል፦ 21:10 *ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደ እናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አትገነዘቡምን*? لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَٰبًۭا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
“አትገነዘቡምን?” የሚለው ቃላት በአጽንዖትና በእንክሮት ልናጤነው የሚገባ ሃይለ ቃል ነው፤ ቁርአን ክብራችን በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ነው፤ አዎ የሰው ልጆች ሊከብሩበት የሚችሉበት ጥበብ ይዟል።
ነጥብ ሁለት
- “ነቅል” -
“ነቅል” نفل ማለት “አስተርዮ”epiphany” ማለት ሲሆን “ወሕይ” وَحْى ነው፤ አምላካችን አላህ ወደ ነብያችን””ﷺ”” ጥበብን አውርዷል፦ 4፥113 አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና *ጥበብን* አወረደ፡፡ *የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا
ይህም ጥበብ ክብራችን በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ቁርአን ነው፤ ቁርአን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ ነው፦ 10፥1 “አሊፍ ላም ራ” ይህቺ *ጥበብ* ከተመላው መጽሐፍ ከቁርኣን አንቀጾች ናት፡፡ الٓر ۚ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ 30፥2 ይህች *ጥበብ* ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ 36፥2 *ጥበብ* በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡ وَٱلْقُرْءَانِ ٱلْحَكِيمِ
ስለዚህ ክብራችን በውስጡ ያለበትን ይህንን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ መገንዘብ ግድ ይላል ማለት ነው፤ የእሳት ሰዎች “የምናገናዝብ” በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ብለው ይፀፀታሉ፦ 67:10 የምንሰማ ወይንም *”የምናገናዝብ”* በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ይላሉ። وَقَالُوا۟ لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِىٓ أَصْحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ
(✍ከወንድም ወሒድ ዑመር)