ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
(ከMain Page የተዛወረ)
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዛሬ ሐሙስየካቲት 29 ቀን 2004
( 8 ማርች, 2012 እ.ኤ.አ. )ነዉ።
Wikibar.png
መቅድም።                       
መቅድም።                       
      ውክፔዲያ ማለት የተለያዩ አገር ሰዎች ተሰባስበው በብዙ ቋንቋዎች የዓለምን ዕውቀት እየመዘገቡ እና እያነበቡ ያሉበት በጣም ታዋቂ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ማንም ሰው በዚህ መዝገበ ዕውቀት ሊጽፍ ይችላል። እርስዎ ለውክፔዲያ አዲስ ከሆኑ እታች ለጀማሪዎች የሚለውን አፅቅ ይጫኑና እንዴት እንደሚሳተፉ ይማሩ።

እዚህ ውክፔዲያ ላይ ጽሑፍ ለማቅረብ፡

  • ይድፈሩ -- አዲስ ጽሑፍ ለመጀመር ወይንም ያለውን ጽሑፍ ለማስተካከል ምንጊዜም አይፍሩ። ጽሑፍዎ ያልተሟላ፣ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢመስልወ አይጨነቁ። ጅምር ጽሑፍዎ በተፈለገው ጊዜ ሊስተካክል፣ ሊሻሻል እና ሊጠናቀቅ ይችላልና።
  • ይማሩ ያስተምሩ -- የሚጽፏቸው ጽሑፎች ሌሎችን የሚያስተምሩ ብቻ ሳይሆኑ እራስዎንም እሚያስተምሩ እንዲሆኑ ይጣሩ።
  • ይተርጉሙ -- ጽሑፍ ለማቅረብ የግዴታ ከባዶ መነሳት አያስፈልግም። ከእንግሊዝኛው ውክፔዲያ ወይም ከሌላ ቋንቋ ውክፔዲያም እየተረጎሙ ጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ።
ዜና ውሎ.png
ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።    
ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።    

የካቲት ፳፱

  • ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - ‘ቴሌፎን’ ተብሎ የተሠየመው ፈጠራ የአዕምሯዊ ንብረትነቱ (patent) በአሌክሳንደር ግራሃም ቤል ስም ተመዘገበ።
Deco pag5.svg
Pot de peinture.gif
የዕለቱ፡ምርጥ፡ምስልና፡አዳዲስ፡ጽሑፎች።
የዕለቱ፡ምርጥ፡ምስልና፡አዳዲስ፡ጽሑፎች።

Green Flag West 11-08.jpg A U.S. Air Force F-15 Strike Eagle with the 335th Fighter Squadron, Seymour Johnson Air Force Base, N.C in Nevada, US

ትኩስ ሻይ አይከን.svgመጨረሻ የቀረቡ 3 ትኩስ መጣጥፎች

Lgo1.png
የመደቦች፡ዝርዝር።                  
የመደቦች፡ዝርዝር።                  
Star with shadow.svg
የዕለቱ፡ምርጥ፡ፅሑፍ።
የዕለቱ፡ምርጥ፡ፅሑፍ።

ዛር-----------

ባለዛር ግብጽ.jpg

ዛር በምስራቅ አፍሪካ፣ በተለይ በኢትዮጵያና ሱዳን አካባቢ የተለመደ የመንፈሶች ስብስብ እና በዚህ ስብስብ ዙሪያ ያለ ዕምነትና ተግባር ነው። በተመሳሳይ መልኩ የዛር እምነት የግሪክ እና ሮሜ ወረራ ሰለባ ባልሆኑት የግብጽ ክፍሎች፣ በተለይ በደቡባዊ ግብጽ የሚዘወተር ነው። ከዚህ በተረፈ የዛር እምነት በጅቡቲኤርትራሶማሊያ፣ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢራን ድረስ የዛር እምነት፣ በብዙ ዓይነት ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ሲሰራበት ይታያል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ዛር፣ ለሚያምኑት ሰዎች፣ የማይታይ ግን የወደፊቱን ማየት የሚችል፣ የዓለምን ችግር ሊፈታ እስኪችል ሃይል ያለው፣ ከስጋ ደዌ በሽታዎች ውጭ ማናቸውንም በሽታዎች ማዳን የሚችል፣ በአንጻሩ ደግሞ የማያከብሩትን ሰዎች መጉዳት፣ መግደልና ማጥፋት የሚችል መንፈስ ነው።

የአእምሮ በሽታ

ሆኖም ግን ይህ የዛር መንፈስ ብዙ ጊዜ የሚታየው በድሃውና በተጨቆነው የህብረተሰብ ክፍል ነው። ተመራማሪዎች ከዚህ ተነስተው የዛር መንፈስ የሚመጣው ከመጨቆን፣ ክበታችነት ስሜት፣ እንዲሁም የፍላጎት አለሟሟላት ከሚፈጥረው የአእምሮ ቀውስ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ በዚሁ በሽታ ሲጠቁ ይታያሉ። ደቡባዊ ግብጽም ውስጥ ሴቶች ለዛር የበለጠ ተጠቂ እንደሆኑ ይጠቀሳል። እስራኤል አገር ያሉ ሃኪሞች የዛር በሽታን ከሳይንስ አንጻር በቀላሉ ሊያክሙት እንደቻሉ ጥናታቸው ያስረዳል ። በእስራኤል አገር የሴቶች መብት የመከበር ሁኔታ ሲታይ በዛር የሚጠቁ ኢትዮጵያውያን እንደቀደሞው አብዛኞቹ ሴት ከመሆን ይልቅ ወንዶቹም ሴቶቹም እኩል የመጠቃት ሁኔታ አሳይተዋል።

ዛር በባለ-ዛሮች እይታ

የዛር አመጣጥ አፈ ታሪክን አጥኝው ራይደልፍ ሞላቨር መዝግቦት ይገኛል። እንደ አፈ ታሪኩ አገላለጽ፣ አዳም እና ሔዋን ከገነት ከተባረሩ በኋላ 30 ጥንድ ልጆች የነበሯቸው ሲሆን አንድ ቀን እግዚአብሔር ሊጠይቃቸው ሲመጣ 15ቶቹን እና ቆንጆ የሆኑትን ልጆቻቸውን በዋሻ ደብቀው 15ቱን ጥንድ ብቻ ለእግዚአብሔር አሳዩ። እግዚአብሔርም በማዘን ዋሻው ውስጥ ያሉት 30ዎቹ ቆንጆ ልጆች እስከ ዘላለሙ እማይታዩ ይሁኑ ብሎ ተራገመ። እኒህ እንግዲህ የዛር መንፈስ ወይንም ዛር ሆኑ።

እንደ አፈ ታሪኩ እንግዲህ ዛሮች የሰው አይነቶች እንጂ አጋንንቶች አይደሉም። እንደሰው ሁሉ፣ ገሚሶቹ ዛሮች ጥሩ ሲሆኑ ገሚሶቹ ደግሞ መጥፎ ናቸው። የዛር አለቆች እርስ በርሳቸው ሲዋለዱ ሃይለኛ ዛር ሲወልዱ ዛሮችና የዛር አሽከሮቻቸው ሲዋለዱ ደግሞ የዛር ውላጅ ይፈጥራሉ፡፡ በአፈ ታሪኩ መሰረት እነዚህ የዛር ውላጆች ሃይላቸው አነስተኛ ነው ማለት ነው። ዛር ጠሪዎች ዛሮችን በስማቸው ሊያውቁዋቸው ይችላሉ፤ ከነዚህ ስሞች ውስጥ ጠቋር፣ ግራኝ፣ አንበሶ፣ ከድር... ይጠቀሳሉ ።

አፈ ታሪኩ የዛርን ወደኢትዮጵያ መምጣት በዓፄ ካሌብ ዘመን ያደርገዋል። ዓፄ ካሌብ ስልጣናቸውን ሲለቁ ዓፄ ገብረ መስቀልን የሚታየው አለም ንጉስ አርገው ሾሙ። የገብረ መስቀልን ወንድም ወልደ እስራኤልን ደግሞ የማይታየው አለም (የዛሩ አለም) መሪ አድርገው ሾሙ። ወለተ እስራኤል እንግዲህ እስካሁን ዘመን የመንፈሳዊው አለም ገዢ ነው ።
[[|]]
Wikibar.png
Wikibar.png
ይጠይቁ፣ ይሳተፉ !!!
ይጠይቁ፣ ይሳተፉ !!!

ስለ ምን ለማወቅ ይፈልጉ ነበር?በዚህ ያቅርቡ።ቀልዶችን እዚህ ላይ ይጨምሩ!

can't see the Amharic font?

Click here to download the Amharic Unicode.
Wikimedia-logo.svg
የሥራ፡እህቶች።
የሥራ፡እህቶች።

ነጻ መጽሐፈ ዕውቀት የሆነው የውክፔዲያ አስተናጋጅ Wikimedia Foundation ነው። ይህ ለማትረፍ ያልሆነ ድርጅት አያሌ ልዩ ልዩ ባለ ብዙ ቋንቋ እና የጋራ ጥቅም ሥራ እቅዶች ያካሂዳል፦

Wiktionary
መዝገበ ቃላት
Wikibooks
ነፃ መጻሕፍት
Wikiquote
የጥቅሶች ስብስብ
Wikisource
ነፃ የደራሲ ስራዎች
Wikispecies
የፍጡሮች ማውጫ
Wikinews Wikinews
ወቅታዊ ዜናዎች
Commons
የጋራ ሚዲያ ማስቀመጫ
Meta-Wiki
ውኪሜድያ ጠቅላላ ዕቅዱ የጋራ መተባበር


[[|]]
የኔ መሣርያዎች

Variants
Actions
የማውጫ ቁልፎች
ጠቃሚ መሣሪያዎች
በሌሎች ቋንቋዎች