Jump to content

ሀዲያ (ታሪካዊ ክልል)

ከውክፔዲያ

ሀድያ ወይም አደላ በ መካክለኛው ክፍለ ዘመን በ ደቡብ እትዮጵያ ውስጥ ከ ሽዋ በስተ ሰሜን እና ከ ሻራካ በስተ ደቡብ የሚገኝ የ ሙስሊም ግዛት ነበር። የ ሀድያ የ ሙስሊም ግዛት ነዋሪዎች በ ዋነኝነት የ ኩሺቲክ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ማለትም የ ሀድያሃላባ እና ቀበና ማህበረሰብን እንዲሁም እንደ ስልጤ እና ሀረር ያሉ የ ሴሜቲክ ቋንቋ ተናጋርዎች ናችው። ሀድያ በ ታሪክ ውስጥ የ አዳል ሱልጣኔት ግዛት ነበረች በመቀጠልም በ አስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን በ አቢሲንያ መንግስት ስር ራስ ገዝ ክልል ሆና መቆየት ችላለች። በ አስራ ስድስተኞቹ ሀድያ ነጻነቷን አግኝታ በ ጋራድ ትመራ ነበር።