Jump to content

ሃይማኖት አለሙ

ከውክፔዲያ

ረዳት ፕሮፌሰር ኃይማኖት ዓለሙትወና /አክቲንግ/ በአሜሪካን አገር Minnesota University በሁለተኛ ዲግሪ ተምሯል፡፡ በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲራክማኖቭ ኮሌጅ ትወናን አስተምሯል፡፡ የሲሳይ ንጉሱን ልቦለድ /ግርዶሽ/ ወደ ፊልም በመቀየር አዘጋጅቷል፤ ተውኗል፡፡ የሼክስፒርን ስራዎች በተለይም በጫንያለው ወልደጊዮርጊስቴዎድሮስ ተሰማ የተተረጎመውን ተጫወቷል፡፡ በተለይም በፀጋዬ ገብረ መድህን ስራዎች በዘመኑ እጅግ ድንቅ ብቃት ያሳየባቸውን የእናት ዓለም ቀኑ እና ሀሁ በስድስት ወር ቴአትሮች ገፀባህሪያት በብሔራዊ ቴአትር ተውኗል፡፡ ሀምሌትን አዘጋጀቷል፡፡ ከፍቃዱ ተክለማሪያም በፊት ቴዎድሮስን ሆኖ ተወኗል፡፡ ጊታር በድንቅ ብቃት ይጫወት ነበር፡፡ በሲዲ ያልተለቀቁ የእንግሊዝኛ ዘፈኖች አሉት፡፡ ከምንም በላይ ግጥም በማራኪ አቀራረብ በማንበብ ይወደድ የነበረው አነጋፋው አርቲስት ሀይማኖት ዓለሙ በመድረክ መምራትም ተወዳጅ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማስታወቂያው ዘርፍ ተሰማርቶ እየሰራ የነበረው ሀይማኖት ባደረበት ህመም መስከረም 92007 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡