ሉኩስ
Appearance
ሉኩስ በ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና ማዋዕል ዘንድ፣ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ስምንተኛ ንጉሥ ነበረ። የ2 ባርዱስ ተከታይ ሲሆን ለ30 ዓመት (ምናልባት 2016-1986 ዓክልበ. ግድም) እንደ ነገሠ በሌላ አፈታሪካዊ ምንጭ ተብሏል።
ሉኩስ ፓሪስ የተባለውን ከተማ እንደ መሠረተ በአንዳንድ ደራሲ ይታስባል። ይህ ከተማ ከሮሜ መንግሥት ዘመን አስቀድሞ ፓሪሲ የተባለው የኬልቶች ጎሣ ዋና ከተማቸው ሉኮቶኪያ ሆኖ ነበር። እንዲሁም ሌውኪ (ወይም «ሉከንሴስ») የተባለው የኬልቶች ጎሣ እን ዋና ከተማቸው ቱል ከሉኩስ ጋራ ግንኙነት እንዳላቸው በአንዳንድ ጸሐፊ ዘንድ ይታመናል።
በሌላ መጽሐፍ በኩል ሉኩስ አዳኝ ሲሆን በማደን እያለ ቤቱን በሴን ወንዝ ደሴት (የአሁን ፓሪስ ሥፍራ) ላይ ሠርቶ ነበር። ከዚያም በላይ ለዝ-አን-ኤኖ የሚባለውን ቦታ በአሁኑ ቤልጅግ እንደ መሠረተ ይላል።[1]
በብዙ ምንጮች ዘንድ ሉኩስ የ፪ ባርዱስ ልጅ ነበረ፤ የሉኩስም ልጅና ተከታይ ኬልቴስ ሆነ። አንዳንድ መጽሐፍ ግን ኬልቴስ የባርዱስ አንድያ ሕጻን ልጅ ስለ ሆነ አካለ መጠን እስከሆነበት ወቅት ድረስ ሉኩስ በእንደራሴነት ገዛ ይለናል።[2]
ቀዳሚው 2 ባርዱስ |
የሳሞጤያ (ጋሊያ) ንጉሥ 2016-1986 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ) |
ተከታይ ኬልቴስ |