2 ባርዱስ

ከውክፔዲያ

2 ባርዱስ (ትንሹ ባርዱስ) በ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና ማዋዕል ዘንድ፣ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ሰባተኛ ንጉሥ ነበረ። የሎንጎ ልጅና ተከታይ ሲሆን ለ37 ዓመት (ምናልባት 2053-2016 ዓክልበ. ግድም) እንደ ነገሠ በሌላ አፈታሪካዊ ምንጭ ተብሏል።

ሎንጎ እና ልጁ 2 ባርዱስ አብረው ሎንጎባርዲ የተባለውን ወገን እንደ መሠረቱ የሚያምኑ ጸሐፊዎች አሉ። ሆኖም ሎንጎባርዲ እራሳቸው በጻፉት ታሪክ መጻሕፍት ዘንድ፣ መጀመርያ ከስካንዲናቪያ ወጥተው ሎንጎባርዲ ወይም «ረጅም ጺሞች» ከተባሉ በኋላ ነው በስሜን ጣልያን በ6ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የሠፈሩ። ስለዚህ ሎንጎባርዲ ከሎንጎ እና ከባርዱስ እንዳልተሰየሙ የስሞቹም ተመሳሳይነት አጋጣሚ እንደ ሆኑ የሚጽፉም አሉ።

በትንሹ ባርዱስ ዘመን የኦጊጌስ ጐርፍ በግሪክ አገር ስለ ደረሰ፣ አዲስ ከተማ የኦጊጌስን ስም ለማስታወስ «ቦርግ-ኦጊጌስ» እንደ ተሠራ የሚሉ መጻሕፍት አሉ፣ ይህም የአሁን ቡርዥ፣ ፈረንሳይ ማለት ነው። ከዚህ ሌላ ልማድ ቦርዥ በዚህ ዘመን ተሠርቶ ቢሆንም ስያሜ ከባርዱስ ስም ግንኙነት እንዳለው ይላል።[1]

በብዙ ምንጮች ዘንድ ከባርዱስ ቀጥሎ ልጁ ሉኩስ ተከተለው። አንዳንድ መጽሐፍ ግን የባርዱስ አንድያ ልጅ ኬልቴስ ሕጻን ስለ ሆነ አካለ መጠን እስከሆነበት ወቅት ድረስ ሉኩስ በእንደራሴነት ገዛ ይለናል።[2]

በዚህ ዘመን ፈርዖን ኦሲሪስ አፒስ የልጁን ኔፕቱን ልጅ አልቢዮን በታላቅ ብሪታንያ ደሴት ላይ፣ የኔፕቱንም ሌላ ልጅ ቤርጊዮንአየርላንድና በኦርክኒ ደሴቶች ላይ ሾማቸው፤ ይህን ሁሉ ከባርዱስ ግዛት ያዙ።

ቀዳሚው
ሎንጎ
የሳሞጤያ (ጋሊያ) ንጉሥ
2053-2016 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሉኩስ
  1. ^ የ1677 ዓም ፈረንሳይኛ ታሪክ
  2. ^ የ1642 ዓም ፈረንሳይኛ ታሪክ