Jump to content

ዖጊጌስ

ከውክፔዲያ
(ከኦጊጌስ የተዛወረ)

ዖጊጌስ (ግሪክኛὨγύγης /ኦጊውጌስ/) በግሪክ አፈ ታሪክ የጥንት ንጉሥ ሲሆን ብዙ ጊዜ የቦዮቲያ ንጉሥ ይባላል፣[1] በሌላ ልማድ ግን የአቲካ መጀመርያ ንጉሥ ነበረ።

«የዖጊጌስ ጎርፍ»

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ቦዮቲያ በጥንታዊ ግሪክ አገር። ከኮፓይስ ሐይቅ እስከ አቲካ ድረስ በአፈታሪክ «የኦጊጌስ ጎርፍ» የደረሰበት ነው።

ከአቲካ ዙሪያ የነበረው አገር ከነቦዮቲያ አንዳንዴ ግራይኬ ይባል ነበር። በዚህ አገር በዖጊጌስ ዘመነ መንግሥት «የዖጊጌስ ጎርፍ» በአገሩ ላይ እንደ ደረሰ ይተረካል።

የቀድሞ ቤተ ክርስቲያን መምህር ዩሊዩስ አፍሪካኑስ (፫ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም) ደግሞ እንደ ጻፈው፣ «ይህ ጎርፍ በአቲካ ሆነ፣ ፎሮኔዎስአርጎስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ አኩሲላዎስ እንደሚተርክ።» ይኸውና አንዳንድ ሌሎች ምንጮች 2059 ዓክልበ. ግድም የሚመስል ጊዜ ያጠቁማል፤ በሌላ ግን እጅግ ይለያል ለምሳሌ በፕላቶ ግመት ጎርፉ በ9500 ዓክልበ. ተከሠተ[2] ወይም በቫሮ ዘንድ በ2144 ዓክልበ. ነበር፤ በአፍሪካኑስም ግመት በ1801 ዓክልበ. ሆነ፤ በተጨማሪ በሙሴ ዘመን እንደ ነገሠ ያምናል።[3]

እንደ ትውፊቱ ንጉሥ ዖጊጌስ ከጥፋት ውኃው አመለጠ፤ ብዙዎች ግን ጠፍተው ነበር። ዖጊጌስ ካረፈ በኋላ፣ ከጎርፉ ጉዳት የተነሳ አቲካ ለ189 ዓመታት እስከ ኬክሮፕስ ዘመን ድረስ ያለ መንግሥት ቀረ።[4]

በግሪክ አፈታሪክ ሁለት ታላቅ ጎርፎች የተመዘገቡ ናቸው፤ ከ«ኦጊጌስ ጎርፍ» በቀር ሌላ «የዲውካልዮን ጎርፍ» የሚለው አፈታሪክ አለ።

ልዩ ልዩ ምንጮች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፓውሳኒዮስ (፪ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም) እንደሚጽፈው፣ ኦጊጌስ የኤክቴነስ ብሄር መሪ ሆኖ የጤቤስ ከተማ (በቦዮቲያ) መስራች ነበርና ግዛቱ ስለርሱ «ዖጊጊያ» ተብሎ እርሱ መጀመርያው ንጉሡ ሆነ።

ስቴፋኑስ ቢዛንቲዮስ (፮ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም) ግን ኦጊጌስ የሉቅያ መጀመርያ ንጉሥ ነበር። አፍሪካኑስ ደግሞ ኤሌውሲስ የተባለውን ከተማ እንደ መሠረተ ይለናል።[3]

ፍላቪዩስ ዮሴፉስ ዘንድ ግን፣ «ዖጊጌስ» አብርሃም አጠገቡ የተቀመጠበት የኬብሮን በሉጥ ዛፍ ስያሜ ነበር።[5]

  1. ^ Entry "Ogygus" in N. G. L. Hammond and H. H. Scullard, The Oxford Classical Dictionary, Second Edition, Oxford University Press: 1970.
  2. ^ ቲማዮስ (22), ክሪቲያስ (111-112), and ሕጎቹ ጥራዝ III ይዩ።
  3. ^ Africanus, Chronography, quoted in Eusebius, Praeparatio Evangelica, 10.10.
  4. ^ Gaster, Theodor H. Myth, Legend, and Custom in the Old Testament, Harper & Row, New York, 1969.
  5. ^ Josephus. Antiquities of the Jews. Book I. Chapter 10. Verse 4. Retrieved from: http://sacred-texts.com/jud/josephus/ant-1.htm