ሎንጎ

ከውክፔዲያ

ሎንጎ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና ማዋዕል ዘንድ፣ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ስድስተኛ ንጉሥ ነበረ። የባርዱስ ልጅና ተከታይ ሲሆን ለ23 ዓመት (ምናልባት 2076-2053 ዓክልበ. ግድም) እንደ ነገሠ በሌላ አፈታሪካዊ ምንጭ ተብሏል።

ሎንጎ ላንግረ የተባለውን ከተማ እንደ መሠረተ በአንዳንድ ደራሲ ይታስባል። ይህ ከተማ ከሮሜ መንግሥት ዘመን አስቀድሞ ሊንጎናውያን የተባለው የኬልቶች ጎሣ ዋና ከተማቸው አንደማንቱኑም (ወይም ሊንጎኔስ) ሆኖ ነበር። ደግሞ ናሙር ከተማ (በቤልጅግ) መመሥረቱ በአንዳንድ ምንጭ ይጻፋል።[1]

በብሪታንያ፣ ጀርመን እና ስሜን ጣልያን እንደ ዘመተ የሚል ልማድ አለ። በተጨማሪ ሎንጎ እና ልጁ 2 ባርዱስ (ትንሹ ባርዱስ) አብረው ሎንጎባርዲ የተባለውን ወገን እንደ መሠረቱ የሚያምኑ ጸሐፊዎች አሉ። ሆኖም ሎንጎባርዲ እራሳቸው በጻፉት ታሪክ መጻሕፍት ዘንድ፣ መጀመርያ ከስካንዲናቪያ ወጥተው ሎንጎባርዲ ወይም «ረጅም ጺሞች» ከተባሉ በኋላ ነው በስሜን ጣልያን በ6ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የሠፈሩ። ስለዚህ ሎንጎባርዲ ከሎንጎ እና ከባርዱስ እንዳልተሰየሙ የስሞቹም ተመሳሳይነት አጋጣሚ እንደ ሆኑ የሚጽፉም አሉ።

ቀዳሚው
ባርዱስ
የሳሞጤያ (ጋሊያ) ንጉሥ
2076-2053 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
2 ባርዱስ
  1. ^ [1]