ባርዱስ

ከውክፔዲያ

ባርዱስ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና ማዋዕል ዘንድ፣ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) አምስተኛ ንጉሥ ነበረ። የድሩዊስ ልጅና ተከታይ ሲሆን ለ62 ዓመት (ምናልባት 2139-2077 ዓክልበ. ግድም) እንደ ነገሠ በሌላ አፈታሪካዊ ምንጭ ተብሏል።

ባርዱስ ለሙዚቃና ለቅኔ የነበረው ፍቅር የገነነ ሲሆን ከስሙ «ባርድ» ለሚባለው አዝማሪና ባለቅኔ አይነት ትምህርት በኬልቶች መካከል እንደ መሠረተ ተጽፏል።

ቀዳሚው
ድሩዊስ
የሳሞጤያ (ጋሊያ) ንጉሥ
2139-2077 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሎንጎ