ድሩዊስ

ከውክፔዲያ

ድሩዊስ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና ማዋዕል ዘንድ፣ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) አራተኛ ንጉሥ ነበረ። የሳሮን ተከታይ ሲሆን ለ14 ዓመት (ምናልባት 2153-2139 ዓክልበ. ግድም) እንደ ነገሠ ተብሏል። ዜና መዋዕሉ በሙያ የተመላ ይለዋል፤ አኒዩስም ባቀረበው ሓረግ ዘንድ አባቱ የሳሮን ልጅ ናምኔስ ነበረ። በሻርትረ አካባቢ በድርው ኮሌጅ ሠርቶ የድሩዊዶች ሥርዓት መስራች እንደ ሆነ ይታመን ነበር። በሻርትረ ዙሪያ ደግሞ በጥንት የተገኘው ካርኑቴስ ወገን አባት እንደ ነበር ተጽፏል።

ቀዳሚው
ሳሮን
የሳሞጤያ (ጋሊያ) ንጉሥ
2153-2139 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ባርዱስ