ላው ድዙ

ከውክፔዲያ
ላው ድዙ ወደ ምዕራቡ በጎሽ ጀርባ ሲሄድ

ላው ድዙ6ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ያህል የቻይና ፈላስፋ ነበር። የዳዊስም መሥራችና የእምነት ጽሑፉ የዳው ዴ ጂንግ («የምግባር መንገድ ጽሑፍ») ደራሲ ነበር። በኋላ (ከ2ኛ ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ጀምሮ) በዳዊስም ውስጥ እንደ አንድ አምላክ ተቆጥሯል።

ልክ መቼ እንደ ኖረ በእርግጥ ባይታወቅም በኮንግ-ፉጸ ዘመን ያሕል (6ኛው ክፍለ ዘመን ክክርስቶስ በፊት) እንደ ነበር ይታመናል። (እንዲሁም ይህ በሕንድ አገር የኡዲስም መሥራች ጎታማ ቡዳና የጃይኒስም መስራች ማሃቪራ ዘመን ያሕል ነበር።) በዳዊስቶች ዘንድ፣ ላው ድዙ እና ኮንግ-ፉጸ አንዴ ተገኛኑ።

ላው ድዙ የመዝገብ ጽሑፍ ዘጋቢ እንደ ነበር ይባላል። በአንዳንድ አቆጣጠር በ610 ዓክልበ ግድም ተወለደ፣ መጽሐፉን የጻፈው 540 ዓክልበ. ያሕል ነበር። ቅጂዎች ቢያንስ ከ300 ዓክልበ. ጀምሮ እንደ ተገኙ ከሥነ ቅርስ እርግጥኛ ነው።

በፍልስፍና መጽሐፉ ዳው ዴ ቺንግ ከጻፈው በተለይ ታዋቂ የሆነው የዳዊስም «ሦስት ሀብቶች» (ቆጠባ፣ ምሕረት፣ ትሕትና) ናቸው። ከላው ድዙም አስቀድሞ ለእስራኤል ነቢይ ሚክያስ (700 ዓክልበ. ግድም) በትንቢተ ሚክያስ 6:8 በጣም ተመሳሣሳይ መልዕክት ተሰጠ፤ በዚያ መሠረት በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ ሦስቱ አስፈላጊነቶች ፍርድ፣ ምሕረትና ትሕትና ናቸው።