ሐምሌ ፳፫

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ሐምሌ ፳፫

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፳፫ ኛው ዕለት ነው።

ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፵፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፵፪ ዕለታት ይቀራሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ስማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ታስባለች።


ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፯፻፶፬ ዓ/ም የዛሬዋ የኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ተመሠረተች።

፲፮፻፳፩ ዓ/ም ናፖሊ በተባለች የምዕራብ ኢጣልያ ከተማ በመሬት ነውጥ ፲ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

፲፰፻፺፩ ዓ/ም - የሐረር ከተማ የመጀመሪያው የመድኀኒት መደብር፤ ዛፊሮፖፑሎ በተባለ ግሪክ ‘ፋርማሲ ኢትዮፕዬን’በሚል ስም ተከፈተ።

፲፱፻፫ ዓ/ም ደጃዝማች ተፈሪ መኮንን እና ወይዘሮ መነን አስፋው በዚህ ዕለት ተጋቡ።

፲፱፻፳፪ ዓ/ም በኡራጓይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር ዋንጫ ውድድር አስተናጋጇ ኡራጓይ ዋንጫውን ዋና ከተማዋ ሞንቴቪዲዮ ላይ አሸነፈች።

፲፱፻፵፰ ዓ/ም ፕሬዚደንት አይዘንሃወርአሜሪካ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት" (House of Representatives) እና "የእንደራሴዎች ሸንጎ" (Senate) በአንድነት ያጸደቁትን “በእግዚአብሔር እናምናለን” ("In God We Trust”) የሚለውን የአገሪቱን ብሔራዊ መፈክር ሕግ ፈረሙ።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]