ቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ቅዱስ ጊዮርጊስ (272-295 ዓም) በታሪካዊ ሰነዶች መሠረት በሮሜ መንግሥት በቄሣሩ ዲዮክሌቲያን ዘመን የነበረ አንድ ክርስቲያን ወታደር ነበር። በዚህ ዘመን ክርስትና በሮሜ መንግሥት ሕግጋት ተከለከለ። ግን በሕዝቡ ዘንድ እንዲሁም በወታደሮች ዘንድ ወንጌል እየተስፋፋ ነበር። በ295 ዓም በዲዮክሌቲያን ትዕዛዝ ወታደሮች ሁሉ ኢየሱስን ለመካድ፣ ለአረመኔ ጣኦት ለመሠው፣ ወይም ለመገደል ተገደዱ። ጊዮርጊስ የተወደደ መኮንንና የንጉሥ ወታደር ሲሆን ለንጉሡ ፊት እምቢ አለው። ስለዚህ እጅግ አሰቃዩት፣ ሆኖም እስከ ሞቱ ድረስ ኢየሱስን ከቶ አልካደም። ነገር ግን በዚህ ወቅት ብዙ የዋሆች ወንዶችም ሴቶችም በገሃድ ተሰቃዩና የሰዎች ስሜት ከንጉሦቹ ጨካኝ ሃይማኖት ወደ ክርስትና በጅምላ እየተዛወረ ነበር። ከጥቂት አመታት በሗላ ክርስትና በሕግ ተፈቀደ፤ በመቶ ዘመን ውስጥ ክርስትና ብቻ በሮማ የመንግሥት ሃይማኖት ሆነ።

ከዚህ በኋላ የጊዮርጊስ ስም በክርስቲያኖች ዘንድ በጣም ዘመናዊ ሆነ፤ በክርስትና እስካሁን ብዙ ቀሳውስት እና ምእመናን «ጊዮርጊስ» ተብለዋል። ከዚህ በላይ እንደ ብዙ አገራት አቃቤ በልማድ ይቆጠራል። የክርስቲያኑን ወታደር የጊዮርጊስን ታሪክ ትዝ ሲሉ፣ ከሌሎች ጥንታዊ አፈ ታሪኮች ጋራ ተዛበ፤ ስለዚህ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘንዶ በመግደል ሳዱላን አዳነ በማለት ጨምረዋልና ይህ አፈ ታሪክ በመላው ዓለም ተሰማ። ዳሩ ግን ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚታወቀው በቤይሩት አገር በየተወሰነ ጊዜ ስው የሚገበርለትን ዘንዶ በመግደሉ ነው።

ጊዮርጊስ ዘንዶውን ስለ መግደሉ መጀመርያ የተጻፈው በአንድ ጅዮርጅኛ ጽሁፍ ከ1050 ዓም ገደማ ነበር። እንዲሁም በዚያን ወቅት ጊዮርጊስ ዘንዶውን ሲገድል የሚያሳዩ ምስሎች በክርስቲያናዊ ሥነ ጥበብ በሰፊ ይታዩ ጀመር። ይህም በተለይ ከጅዮርጅያአናቶሊያ ተስፋፋ። ሆኖም ከ1050 ዓም አስቀድሞ በወጣው ሥነ ጥበብ ዘንድ፣ ጊዮርጊስ ሳይሆን ሌላ በ295 ዓም የተገደለ ክርስቲያን ሰማዕት ቅዱስ ቴዎድሮስ ቲሮ ዘንዶውን እንደ ገደለ የሚል ተመሳሳይ ትውፊት ይታወቅ ነበር። በማኒኪስም ተጽእኖ በኩል፣ በአለም ፍጥረት የዘንዶ ውግያ እንደ ተከሰተ የሚሉ የባቢሎን፣ የግብጽ ወይም የፋርስ አረመኔ እምነቶች ቀርተው እንደ ተስፋፉ ይቻላል።