ወንጌል

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ወንጌል ኢቫንጌሊዮን ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም የምስራች ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸው ትምሀርቶች የተመዘገቡበት መጽሐፍት ወንጌል በመባል ይታወቃሉ። ወንጌል ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ሲሆን አራት መጽሐፍትን ያጠቃልላል። የማቴዎስ ወንጌልየሉቃስ ወንጌልየማርቆስ ወንጌልየዮሐንስ ወንጌል። እነዚህ ወንጌላት ስማቸውን ያገኙት ከጸሐፊዎቻቸው ሲሆን የያዙት ቃል የኢየሱስ ክርስቶሰን ትወልድ፤ ትምህርት፤ ሞትና ትንሳዔ ነው። ሦስቱ ወንጌላት ማለትም የማቴዎስ፤ የሉቃስና የማርቆስ ወንጌል ተመሳሳይ የሆኑ ብዙ ታምራቶችንና ክስተቶችን ይዘው ይገኛሉ። የዮሓንስ ወንጌል ደግሞ በአብዛኛው ያካተተው የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነትና የአብ ልጅነት የሚያብራራ መልእክት ነው።

ብዙ ምዕራፎችን የያዘው ወንጌል የማቴዎስ ወንጌል ሲሆን ፳፯ ምዕራፎች አሉት። ጥቂት ምዕራፍ ያለው ደግሞ የማርቆስ ወንጌል ነው ይኸውም 16 ምእራፎች አሉት። ወንጌል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ክብር የሚሰጠውና አብዝቶ የሚነበብ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ነው። በቅዳሴ ጊዜ ፤ በሌሊት ጸሎትና በጉባዔያት ወቅት ወንጌል ይነበባል።