ጳውሎስ

ከውክፔዲያ
ቅዱስ ጳውሎስ
መልክተኛው
የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ
ስም መጀመሪያ ሳውል በኋላ ጳውሎስ
የተወለደው ቦታ ተርሴስ በሮሜ መንግሥት
የተወለደበት ዘመን በ፩ኛው ክፍለዘመን ፭ኛው ዓመት
የሚታወቀው በመልክቱ፣ ከይሁድነት ወደ ክርስቲያንነት በመቀየሩ ፣ በሰማዕትነቱ
ያረፈበት ፩ኛው ክፍለ ዘመን ፷፬፣፷፭፣ ፷፯ ዓ.ም. በሰይፍ ተሰይፎ
ሥራው ፀሐፊ ፣ ሰባኪ ፣ የክርስትና ሃይማኖት ፈላስፋ
የሚከበረው በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ
ንግሥ ሐምሌ ፭


ሳውል በብሉይ የወጣለት ዕብራዊ ስሙ ሲሆን ፣ ጳውሎስ በሐዲስ የወጣለት ነው ትርጉሙም ብርሃን ማለት ነው ። በተርሴስ (ዛሬ በቱርክ ውስጥ) ከሚቀመጥ ከአንድ ሸማኔ ተወልዶ ካደገ በኋላ በኢየሩሳሌም ኦሪትን ከገማልኤል ተማረ። ስለኦሪትና ስለሙሴ ከፍ ያለ ቅናት፤ በዘመኑ ስለተፈጠረው የክርስትና ሃይማኖት የበዛ ጥላቻ ነበረው። ስለዚህ ክርስቲያኖችን ማባረር፤ ማሰር፤ ማጉላላት ሥራዬ ብሎ ይዞት ነበር።

ለዚሁ ጉዳይ ወደ ደማስቆ ሲሄድ እከተማይቱ ሊደርስ ሲል የሚያንፀባርቅ ብርሃን መታውና ወደቀ።

ጳውሎስ በደማስቆ መንገድ

በመሬት ላይ እንደተኛ በሰማይ ካለው ከኢየሱስ ጋራ፤ አሳብ ለአሳብ እንደዚህ ሲል ተለዋወጠ።

ኢየሱስ፦ ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ ? ሳውል፦ አንተ ማነህ አቤቱ ? ኢየሱስ፦ እኔ ኢየሱስ ነኝ አንተ የምታሳድደኝ ። በተሳለ ብረት ላይ ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል ። ሳውል፦ ምን እንዳደርግ፤ ትፈቅዳለህ ? ኢየሱስ፦ ወደ ደማስቆ ከተማ ግባ፤ ልታደርገው የሚገባህን ሐናንያ ይነግርሃል ።

የሐዋ፡ሥራ፡ም፡ ፱ ፣ ቁ፡ ፬-፮

በዚህ ዓይነት ጳውሎስ ክርስትናን የተቀበለው ከክርስቶስ ነው ማለት ይቻላል። ዝርዝር ነገር ከሐናንያ ማጥናቱ እርግጥ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፍጹም ክርስቲያን፤ ትጉህ ሐዋርያ ሆነ። ያለ ዕረፍት የግሪኮችና የሮማውያን አማልክት እነዘውስ እነአርጤሚስ የአሶራውያንና የሲዶናውያን አማልክት እነአስታርት እነበዓል የገነኑባቸውን ከተሞች ያለዕረፍት እየዞረ የነዚያን ከንቱነት፤ የክርስቶስን አዳኝነት በቃልም፤ በጽሕፈትም መሰከረ። ለአባቶቹ ለዕብራውያንም በብሉይ ሐዲስ መተካቱን ለመንገር አልፈራም። ስለክርስቶስና ስለወንጌል በኢየሩሳሌም ተገረፈ፤ በቂሣርያ ታሠረ፤ በሮማ በሰይፍ አንገቱን ተቆርጦ ሞተ።

ነገር ግን በደረሰባቸው ከተሞች ሁሉ ክርስቶስን ሳያሳምን ቤተ ክርስቲያን ሳይመሠርት አያልፍም ነበር። ፲፬ መልዕክቶችንሲጽፍ፤ ከኢየሩሳሌም ግሪክ፤ ከግሪክ ሮማ፤ እየተመላለሰ የሐዋርያነት ሥራውን ሲያከናውን ራሱ ድንኳን እየሰፋ የራሱን መሮሪያ ራሱ ይችል ነበር እንጂ ከሰው ድካም የመነጨ ወይንና ምግብ በርሱ፤ ጉሮሮ አላለፉም ማለት ነው። ደንበኛ ሐዋርያነቱን ከሚያስረዱት ከብዙ ሥራዎቹ ውስጥ አንደኛው ይህ ነው።

: