Jump to content

ላሊበላ

ከውክፔዲያ
የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ
ላሊበላ

የአክሱም ሐውልት
ቤተ ጊዮርጊስ
አገር ኢትዮጵያ
ዓይነት ባህላዊ
መመዘኛ c(i)(ii)(iii)
የውጭ ማጣቀሻ 18
አካባቢ** አማራ ክልል
የቅርስነት ታሪክ
ቅርስ የሆነበት ጊዜ 1970  (2ኛ ጉባኤ)
ላሊበላ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ላሊበላ
በኢትዮጵያ የሚገኝ
* በዩ.ኔ.ስ.ኮ ስሙ እንደሰፈረ።
** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል


ላሊበላ በኢትዮጵያ፣ በአማራ ክልል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር የምትገኝ ከተማ ነች። በ12.04° ሰ 39.04° ምዕ ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ከባሕር ጠለል በላይ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላት ስትኾን የሕዝቡም ብዛት ወደ 11,152 ነው። 1 ላሊበላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ከተማዎች መካከል ከአክሱም ቀጥላ በኹለተኛነት ደረጃ የምትገኝ ከተማ ስትኾን፣ ለአብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ዋና የእምነት ማእከል በመኾን ታገለግላለች። የላሊበላ ነዋሪዎች በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው።

የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እረዳትነት እንደተሰሩ የሚታመን ሲኾን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ጸሓፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ ቴምፕላርስ የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል ነገር ግን ማረጋገጫ አልነበረውም። እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተ ክርስቲያኖች አሉ።

ንጉሡ ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘው፣ ሲወለድ በንቦች ስለተከበበ ነው ይባላል። ላል ማለት ማር ማለት ሲኾን፤ ላሊበላ ማለትም -ላል ይበላል (ማር ይበላል) ማለት አንደሆነ ይነግራል። ውቅር ቤተ ክርስቲያናቱን ንጉሡ ጠርቦ የስራቸው ከመላእክት እገዛ ጋር እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይነግራል። በ16ኛው ከፍለ ዘመን አውሮፓዊ ተጓዥ ላሊበላን ተመልክቶ «ያየሁትን ብናግር ማንም እንደኔ ካላየ በፍጹም አያምነኝም» ሲል ተናግሮ ነበር።

በላሊበላ 11 ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲኾን ከነዚህም ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ (ባለ መስቀል ቅርፁ) ሲታይ ውሃልኩን የጠበቀ ይመስላል። ቤተ መድሃኔ ዓለም የተባለው ደግሞ ከሁሉም ትልቁ ነው። ላሊበላ (ዳግማዊ ኢየሩሳሌም) የገና በዓል ታህሳስ 29 በልዩ ኹኔታ ና ድምቀት ይከበራል፣ "ቤዛ ኩሉ" ተብሎ የሚጠራው በነግህ የሚደረገው ዝማሬ በዚሁ በዓል የሚታይ ልዩ ና ታላቅ ትዕይንት ነው።የሚደረገውም ከቅዳሴ በኋላ በቤተ ማርያም ሲኾን ከታች ባለ ነጭ ካባ ካህናት ከላይ ደግሞ ባለጥቁር ካብ ካህናት በቅዱስ ያሬድ ዜማ ቤዛ ኩሉ እያሉ ይዘምራሉ።

11ዱ የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት 1.ቤተ መድኀኔ ዓለም፣ 2.ቤተ ማርያም፣ 3. ቤተ ደናግል፣ 4.ቤተ መስቀል፣ 5. ቤተ ደብረሲና፣ 6.ቤተ ጎለጎታ፣ 7.ቤተ አማኑኤል፣ 8.ቤተ አባ ሊባኖስ፣ 9.ቤተ መርቆሬዎስ፣ 10. ቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል፣ 11. ቤተ ጊዮርጊስ

ኢትዮጵያ

ታሪካዊ ቦታዎች አክሱምላሊበላጎንደርነጋሽሐረርደብረ-ዳሞአዲስ አበባ
አስተዳደራዊ ክልሎችትግራይአፋርአማራኦሮሚያሶማሌቤንሻንጉል ጉሙዝደቡብ ኢትዮጵያሲዳማማዕከላዊ ኢትዮጵያደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያጋምቤላሐረሪአዲስ አበባድሬዳዋ
ቋንቋዎችአማርኛግዕዝኦሮምኛትግርኛወላይትኛጉራጊኛሶማሊኛአፋርኛሲዳምኛሃዲያኛከምባትኛጋሞኛከፋኛሃመርኛስልጢኛሀደሪኛ
መልክዓ-ምድር - • አባይአዋሽራስ-ዳሽንሶፍ-ዑመርጣናደንከልላንጋኖአቢያታሻላ
ከተሞች - የኢትዮጵያ ከተሞች