ትግርኛ
ቋንቋ ትግርኛ በኤርትራና በኢትዮጲያ የሚነገር ቋንቋ ሲሆን የሴማዊ ቋንቋዎች አባል ነው። ትግርኛ በኤርትራ የብሄረ ትግርኛ ኣፍ መፍቻ ቋንቋ ና የሃገሪቷ የስራ ቋንቋ ሲሆን በኢትዮጲያ ደሞ የብሄረ ትግሬ ( ተጋሩ ) ኣፍ መፍቻ ቋንቋ ና 4ኛ ከፍተኛ ተናጋሪ ያለዉ ቋንቋ ነዉ የተናጋሪዎቹ ቁጥር ከ12 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ በኤርትራ ከ7 ሚሊዮን በላይ በትግራይና በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች ይነገራል። በኤርትራ ኣብዛኛዉ የሌላ ቋንቋ ተናጋሬች ትግርኛ እንደ መግባብያ ይጠቀሙበታል።
ቋንቋ ትግርኛ የግዕዝ ፊደል የሚጠቀም ሲሆን በ ኤርትራ ከ 13 ክፍለ ዘመን ጀምሮ የ ብሄረ ትግርኛ ህዝብ ሕግ-እንዳባ የሚባለዉ ሰዉስቱ ግዛታች ሓማሴን: ሰራየ ና ኣከለጉዛይ የሚጠቀሙበት የህግ ስርዓት ተጽፎበታል የመጀመርያዉ የቋንቋዉ ጽህፋ ደም ሕጊ ኣድግና ተገለባ የሚባለዉ የኣከለጉዛይ ሕገ ስርዓት ነዉ[1]።
ፊደል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የትግርኛ ቀለሞች በዓማርኛው ላይ ጥቂት ተጨማሪ ኣሏቸው እንጂ የተቀራረቡ ናቸው። ኣንዳንድ ፀሓፊዎች ግን ከትግርኛ ቀለሞች ውስጥ እነ "ሀ"፣ "ሐ"፣ "ኀ"፣ "አ" እና "ዐ" የራብኦቻቸው ሞክሼዎች መስለዋቸው ተሳስተው ሊቀንሷቸው ኣጥቁረዋቸዋል። እንደ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ገለጻ ግን ሆሄያቱ ሞክሼዎች ስላልሆኑ መብታቸው መከበር ኣለበት ነው።
ደግሞ ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የውጭ መያያዣዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
- [1] The Ethiopic Alphabet by Dr. Aberra Molla በዶ/ር ኣበራ ሞላ
- [2]
- https://am.wiktionary.org/wiki/Wiktionary:የኢትዮጵያ_ሴማዊ_ሷዴሽ - የትግርኛ ቃላት በውክሽኔሪ
- ^ Negash, Abraham, The Origin and Development of Tigrinya Publications, Santa Clara, California2019 p.3