ጣና ሐይቅ
ጣና ሐይቅ ጎጃም ውስጥ ሲገኝ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል። ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። በቁጥር ከ35 በላይ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥም 22ቱ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት ናቸው። ባንዳንዶቹ ላይም (ለምሳሌ በዳጋ ደሴት) የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች ሲገኙ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ለመጀመሪያ ያስተዋወቀው አቡነ ሰላማ መቃብርም በዚሁ ሃይቅ ይገኛሉ።
የጣና ሃይቅን የሚመግቡ 3ቱ ዋና ወንዞች ርብ፣ ጉማራ ወንዝ ና ትንሹ አባይ በመባል ይታወቃሉ።
የዓሳ ምርት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
አሁን ባለው ይዞታ የጣና ሃይቅ 1,454 ቶን አሳ በአመት ይመረታል። ነገር ግን ይሄ የምርት ሃይቁ ያለምንም ችግር ሊያስተናግድው ከሚችለው 15 በመቶው ያህል ብቻ ነው።
- ደግሞ ይዩ፦ የእንቦጭ አረም
ታሪካዊ የጣና ክፍሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ኢትዮጵያ |
ታሪካዊ ቦታዎች - አክሱም | ላሊበላ | ጎንደር | ነጋሽ | ሐረር | ደብረ-ዳሞ | አዲስ አበባ |
.