ጉዛራ
Appearance
(ከጉዛራ ግምብ የተዛወረ)
ጉዛራ | |
የጉዛራ ቤተ መንግስት | |
የጉዛራ ቤተመንግስት ከእምፍራዝ በስተደቡብ 5ኪሎሜትር ወጣ ብሎ የተሰራ ግምብ ነው። ይሄውም በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ፣ ከጣና ሐይቅ በስተ ስሜን ምስራቅ መሆኑ ነው።
አጼ ሚናስ የክረምት ጊዜን በጉባኤ፣ ጉዛራ አካባቢ ማሳለፍን ልማዳቸው ማድረጋቸው በታሪክ ይጠቀሳል። የጉዛራ ግምብ 18ሜትር በ12 ሜትር ሲሆን፣ በድሮ ዘመን ግምቡን የሚከልል ሰፊ አጥር ነበር። የግምቡ ስራ በ1562ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን አጼ ሠርፀ ድንግል በምጽዋ ቱርኮች ላይ ድል መቀዳጀታቸውን አስመልክቶ ለመታሰቢያነት ያስገነቡት ነበር። [1][2] በ1563ዓ.ም. አጼ ሠርፀ ድንግል የበጌምድርንና የትግሬን አስተዳዳሪዎች በዚሁ ቦታ አነጋግረው እንደነበር በታሪክ ይጠቀሳል።
የጉባኤ ከተማ ከ1570 ጀምሮ እስከ 1581 ድረስ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን ቢያገለግልም በመጨረሻ ግን ንጉሱ ጉዛራን ለቀው ወደሰሜን በማቅናት አይባን ዋና ከተማቸው አደረጉ። የሆኖ ሆኖ የጉዛራ ቤተመንግስት ከጎንደር ከተማ ቀደምት ምሳሌ የሆነ ነበር።
- ^ Monti della Corte, I Castelli di Gondar, 1938, pp. 105-108
- ^ http://iscte.pt/~mjsr/html/expo_jesuits/architecture/guzara_and_dabsan_.htm
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |