Jump to content

ሓዛጋ

ከውክፔዲያ
ሃዘጋ
የሃዘጋ መንደር በ1900 ዓ.ም.
ሃዘጋ is located in ኤርትራ
{{{alt}}}
ሃዘጋ

15°22′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°45′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ሃዘጋ በመካከለኛው ኤርትራ፣ በቀድሞው ሓማሴን ግዛት ስር ያለች አነስተኛ መንደር ናት። ከአሥመራ 13 ማይል ሰሜን ምዕራብ ፣ ከከረን 35 ማይል ደቡብ ምስራቅ ስትገኝ፣ በአካባቢው ሙሉ በሙሎ ትግርኛ ቋንቋ ሲነገር ነዋሪዎቹም በሙሉ ክርስቲያን እንደሆኑ ይጠቀሳል። በሃዘጋ ውስጥ አንድ የካቶሊክ እና አንድ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች በአሁኑ ጊዜ ይገኛሉ።

ሃዘጋ እና ጸዓዘጋ በእርስ-በርስ ፉክክር ሓማሴንን ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምረው እንዳስተዳደሩ ይጠቀሳል። የሓማሴን የመጨረሻው አስተዳዳሪ ከሓዛጋ ሲመነጩ፣ ስማቸውም ደጃዝማች ወልደሚካኤል ሰለሞን ይሰኛል።